መዝሙር (አምላክ አትተወን) March 21, 2021

 አምላክ አትተወን የእጆችህ ሥራ ነን /፪/
 በየቀኑ ወደ አንተ እንጮሃለን
 ዝቅ ብለን እንለምንሃለን

ቀድሞ አባቶቻችን በአንተ ስለ አመኑ /፪/
ታድናቸው ነበር ቆመው ሲለምኑ /፪/

 አምላክ አትተወን የእጆችህ ሥራ ነን /፪/
 በየቀኑ ወደ አንተ እንጮሃለን
 ዝቅ ብለን እንለምንሃለን

አሁን ከመንበርህ ከደጅህ ወድቀናል /፪/
እንደ ቸርነትህ አድነን ብለናል /፪/
አንተዉ አሳልፈው ይህን ክፉ ጊዜ /፪/
እባክህን ስጠን የንስሓ ጊዜ /፪/

 አምላክ አትተወን የእጆችህ ሥራ ነን /፪/
 በየቀኑ ወደ አንተ እንጮሃለን
 ዝቅ ብለን እንለምንሃለን

ይቅር ባይ ነህና ሕዝብህን ተመልከት /፪/
እጅግ በዝቷልና የተዘጋው ቤት /፪/
ዘንባባ ይዘናል እባክህ ዛሬም ና /፪/
ዓለም ተበክሏል አንተው ስጠው ጤና /፪/

 አምላክ አትተወን የእጆችህ ሥራ ነን /፪/
 በየቀኑ ወደ አንተ እንጮሃለን
 ዝቅ ብለን እንለምንሃለን