ከምንም የለንም ወደ ሚሊየን

የቤቶችና እና ሕንፃዎች አስተዳደር ድርጅት አዲስ ሕንጻ ለመሥራት የመሠረት ድንጋይ አኖረ

  • የቤቶችና እና ሕንፃዎች አስተዳደር ድርጅት ከመንግሥት ጋር በመሆን ሕንፃዎችን የማስመለስ ሥራ የሠሩትን አንጋፋ ሰዎች በዕለቱ ሸልሟል

በመምህር ይቅርባይ እንዳለ

ቅድስት ቤተ ክርስቲያንን ካሏት በርካታ ድርጅቶች መካከል ዋነኛውና አንጋፋዉ የልማት ድርጅት የቤቶች እና ሕንፃዎት ድርጅት መሆኑ ይታወቃል፡፡ ከብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ቴዎፍሎስ ዘመነ ፕትርክና ጀምሮ ቤተ ክርስቲያኒቷ የአዲስ አበባ ከተማን ያስዋቡና ለወደፊት የሀገራችን ዕድገት ምሳሌ በመሆን ዱካ የጣሉ ሕንፃዎችን እና ፎቆችን ገንብታለች፡፡

ከምንም የለንም ወደ ሚሊየን ምንም እንኳ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ብትገነባም ከዓመታት በኋላ የደርግ መንግሥት ሀገራችንን ማስተዳደር ሲጀምር ያልለፋበትንና ያልሠራውን መቀማት ልማዱ የሆነው የደርግ መንግሥት የቤተ ክርስቲያንቷን አንጋፋና ምርጥ ሕንፃዎቿን በጉልበት በመቀማት ባዶ እጅ እንድትቀር አድርጓት ነበር፡፡

ለዚህም ነው በመግቢያ ላይ "ከምንም የለን ወደ ሚሊዮን" በማለት በርዕሳችን ለይ ያስቀመጥነው፡፡ ምንም እንኳ የደርግ መንግሥት የቤተ ክርስቲያናችንን አንጡራ ሀብት በመቀማት ቢያጠቃም የኢህአዴግ መንግሥት ሲተካ ግን የቤተ ክርስቲያኒቷን ሕንፃዎች ከመመለስ የቦዘነበት ጊዜ የለም፡፡ ስለዚህ በርካታ የቤተ ክርስቲያን ሕንፃዎችን የኢህአዴግ መንግሥት መልሷል አሁንም በመመለስ ላይ ይገኛል፡፡ በዚህም በዕለቱ በፁዕ አቡነ አረጋዊ መንግሥታችንን ሲያመሰግኑ በአንፃሩም በኃላፊነት ላይ የተቀመጡትን የቤተ ክርስቲያኒቱን አካላት ጠንክረው መሥራት እንዳለባቸው አጽንተው ተናርግረዋል፡፡

ከዚህ በተጨማሪ በሌሎች የአገልግሎት ዘርፎችም ቢሆን መለመድ የሚገባው መልካም ተግባር የቤቶችና እና ሕንፃዎች አስተዳደር ድርጅት ከመንግሥት ጋር በመሆን ሕንፃዎችን የማስመለስ ሥራ የሠሩትን አንጋፋ የድርጅቱ አገልጋዮች በመርሐ ግብሩ ዕለት ሽልማት በመስጠት ምሥጋናውን ገልጾአል፡፡ በዚህ ሥራ ማለትም ቤተ ክርስቲያን ተወስዶባት የነበረውን ሕንፃ በማስመለስ በኩል ከፍተኛ አስተዋጽኦ ካደረጉት ሰዎች መካከል፡-

1ኛ መ/ታ ታደለ ገ/መስቀል
2ኛ መምሬ ተዘራ ወርቁ
3ኛ መጋቤ ካህናት ኃ/ሥላሌ ዘማርያምን በዋናነት ሸልሟል፡፡

የቤችና ሕንፃዎች አስተዳደር ድርጅት ዋና ሥራ አስኪያጅ የሆኑት አቶ ተስፋዬ ውብሸት በዚህ በሽልማት መርሐ ግብሩ ተገኝተው የሽልማቱ መርሐ ግብር አስመልክተው ባደረጉት ንግግር ድርጅቱ ገቢው ወደ 26 ሚሊዮን ማደጉን ገልጸው በይበልጥ ማደግ እንደሚችልና ወደፊትም ሕንፃዎችን የማስመለሱን ሥራ ድርጅቱ በጽናት እንደሚቀጥል ገልጸዋል፡፡
አቶ ተስፋዬ ውብሸት እንደዚህ ዓይነቱን የተሳካና እና ከጊዜ ወደ ጊዜ ዕድገት እያሳየ በመሄድ ላይ ያለውን አርኪና ማራኪ ሥራ በመሥራት ላይ ያሉ በዕውቀት ላይ የተመሠረቱ አስተዳዳሪ በመሆናቸው ልምዳቸውንና አሁን ድርጅቱ ለመሥራት እያሰባቸው ካሉ ከፍተኛ ፕሮጀክቶች አንጻር ለሌላው አስተማሪ እንዲሆን በማካፈል እንዲተባበሩን ጠይቀን በቀጣይ ከእርሳቸው ጋር የምናደርገውን ሰፋ ያለ ቃለ መጠየቅ እናስነብባችኋለን፡፡

 

Read more http://eotcssd.org/the-news/391-2014-09-02-13-19-56.html