በ33ኛው ሀገር አቀፍ አጠቃላይ የሰበካ ጉባኤ ማጠቃላያ ላይ በጉባኤው ፍጻሜ የተደረገው ውይይት

በ33ኛው ሀገር አቀፍ አጠቃላይ የሰበካ ጉባኤ ማጠቃላያ ላይ በጉባኤው ፍጻሜ የተደረገው ውይይት


በ33ኛው ሀገር አቀፍ አጠቃላይ የሰበካ ጉባኤ ማጠቃላያ ላይ በጉባኤው ፍጻሜ የተደረገውን ውይይት እንድናቀርብ በተደጋጋሚ ብዘት ያላቸው የድህረ ገጻችን ተከታታዮች ጥያቄ በማቅረባቸው እና በዕለቱ የነበረውን ውይይት ሁሉንም ሰምቶ እውነቱን እንዲረዳ በማለት እንደሚከተለው አቅርበናል፡፡

...


የሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ የሥርዓተ ትምህርት ማስተማሪያ መጽሐፍ አሳትሞ በቅዱስ ፓትርያርኩ አስመረቀ

የሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ የሥርዓተ ትምህርት ማስተማሪያ መጽሐፍ አሳትሞ በቅዱስ ፓትርያርኩ አስመረቀ

እንደሚታወቀው በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ከተቋቋመ በርካታ ዓመታትን አሳልፏል፡፡ ይሁን እንጂ እስከ አሁን ድረስ የሰ/ት/ቤት ተማሪዎች በግል በተዘጋጀ ጽሑፍና አልፎ አልፎ በግል በሚታተሙ መጽሔቶች እየተማሩ አሁን ላሉበት ደረጃ ደርሰዋል፡፡ ይህ ዓይነቱ ተመሳሳይ ያልሆነ ግንዛቤ እያደር የዕውቀትና የአመለካከት ልዩነት ከመፍጠሩም ባሻገር ለልዩ ልዩ እንግዳ ትምህርቶች በር የከፈተ በመሆኑ የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ...

የ33ኛ የመንበረ ፓትርያርክ አጠቃላይ የሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ ተጀመረ፡፡

ዓመታዊ የሰበካ አጠቃላይ መንፈሳዊ ጉባኤ ዛሬ ተጀመረ ፡፡

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በየዓመቱ የሚካሔደው ዓመታዊ የሰበካ አጠቃላይ መንፈሳዊ ጉባኤ ዛሬ ጥቅምት 5 ቀን 2007 ዓ.ም. ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት፣ ብፁዕ አቡነ ማቴዎስ የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅና የወላይታ ኮንታ ዳውሮ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት፣ የጠቅላይ ቤተ ክህነት የየመምሪያ ኃላፊዎች፣ የሁሉም አህጉረ ስብከት ሥራ አ...

በየዓመቱ የሚከበረው የመስቀል ደመራ በዓል ዘንድሮም በታላቅ ድምቀት ተከበረ፡፡

_DSC8002

በየዓመቱ የሚከበረው የመስቀል ደመራ በዓል ዘንድሮም በታላቅ ድምቀት ተከበረ፡፡

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ከሚከበሩት ታላላቅ ሃይማኖታዊ ብሔራውያን በዓላት ውስጥ ትልቅ መንፈሳዊና ሃገራዊ ፋይዳ ገንዘብ ያደረገውን የመስቀል ደመራ በዓላችን ዘንድሮም በታላቅ መንፈሳዊ ሥነ ሥርዓት በመስቀል አደባባይ በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳሳት ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት፣ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት፣ የአዲስ አበባ ገዳማትና አድባራት አስተዳዳሪዎች፣ ጥንግ ድርብ የለበሱ ሊቃውንተ ቤተ...

ቅዱስ ፓትርያርኩ የመቄዶንያ አረጋውያንና ሕሙማን ጎበኙ

ቅዱስ ፓትርያርኩ የመቄዶንያ አረጋውያንና ሕሙማን ጎበኙ

በቤተ ክርስቲያኗ ስም መቶ ሺህ ብር ለተረጂዎች ድጋፍ አድርገዋል

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት መስከረም 17 ቀን 2007 ዓ.ም ከጥዋቱ በሦስት ሰዓት አረጋውያንና የአእምሮ ሕሙማን ወገኖቻችን ከሚረዱበት በመቄዶንያ አረጋውያንና የአእምሮ ሕሙማን መርጃ ማዕከል ዘንድ በመገኘት ጉብኝትና በቤተ ክርስቲያኒቷ ስም ለመረጃ ማእከሉ ድጋፍ አድርገዋል፡፡

በጉብኝቱ ወቅት የመቄዶንያ መርጃ ማዕከል ቦርድ ሰብሳቢ ክቡ...

መስቀል በቤተ ክርስቲያን አስተምህሮ

መስቀል በቤተ ክርስቲያን አስተምህሮ

መ/ር ፀገዬ ኃይሌ

መስቀል በብዙዎች ሰዎች ኀሊና በብዙ ዓይነትና ቅርጽ የተሰራ ተደርጎ የሚታዩ ወይንም የሚተረጎም ቢሆንም እኛ ግን ከዘመነ ብሉይ መጀመሪያ እስከ ዘመነ ሐዲስ እስከ አለንበት ዘመን ስለአለው ስለክርስቶስ ነገረ መስቀል እንናገራለን የጌታችንና የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ መስቀል አስቀድሞ ከዘመነ አበ ብዙኃን ከአዳም ጊዜ ጀምሮ ብዙ ነቢያት በተለያየ ኅብረ አምሳል ትንቢት የተናገሩለት በዘመነ ሐዲስም እራሱ ኢየሱስ ክርስቶስ በኃጢአት የወደቀውን የሰውን ልጅ ከራሱ ጋር ያስታረቀበት እስከ አሁንም ድረስ...

ዜና ቤተክርስቲያን መስከረም 2007 ዓ.ም

ዜና ቤተክርስቲያን መስከረም 2007 ዓ.ም

zenab2007...

ከምንም የለንም ወደ ሚሊየን

ከምንም የለንም ወደ ሚሊየን

ከምንም የለንም ወደ ሚሊየን

የቤቶችና እና ሕንፃዎች አስተዳደር ድርጅት አዲስ ሕንጻ ለመሥራት የመሠረት ድንጋይ አኖረ

  • የቤቶችና እና ሕንፃዎች አስተዳደር ድርጅት ከመንግሥት ጋር በመሆን ሕንፃዎችን የማስመለስ ሥራ የሠሩትን አንጋፋ ሰዎች በዕለቱ ሸልሟል

በመምህር ይቅርባይ እንዳለ

ቅድስት ቤተ ክርስቲያንን ካሏት በርካታ ድርጅቶች መካከል ዋነኛውና አንጋፋዉ የልማት ድርጅት የቤቶች እና ሕንፃዎት ድርጅት መሆኑ ይታወቃል፡፡ ከብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ቴዎፍሎስ ዘመነ ፕትርክና ጀምሮ ቤተ ክርስቲያኒቷ የአዲስ አበባ ከተማን ያስዋቡና ለወደፊት የሀገራችን ዕድገት ምሳሌ በመሆ...

የዓለም አብያተ ክርስቲያናት ማዕከላዊ ኮሚቴ ስብሰባ በጄኔብ ተካሄደ

የዓለም አብያተ ክርስቲያናት ማዕከላዊ ኮሚቴ ስብሰባ በጄኔብ ተካሄደ

የኢ.ኦ.ተ.ቤተክርስቲያን ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በደሙ የዋጃት በስሙ የመሠረታት ቤተክርስቲያን ናት ከተቋቋመችበት ጊዜ ጀምሮ ብዙ ውስብስብ ችግር ቢያጋጥማትም ተግባሯ ሳይገታ ዓላማዋም ሳይዛነፍ ከዚህ ደረጃ ላይ ደርሳለች ወልድ ዋሕድ የሚለውን ቃል መሠረት አድርጋ አንድ እግዚአብሔር በሦስት ስም በሦስት ግብር በሦስት አካል አንድ አምላክ ወልደ አብ ወልደ ማርያም በተዋሕዶ ከበረ ብላ ታስተምራለች፡፡ ሆኖም በሃይማኖቷና በነጻነትዋ ጸንታ የምትኖር በመሆንዋ ያለፈተና የኖረችበት ጊዜ የለም፡...

ዜና ቤተክርስቲያን ሐምሌና ነሐሴ 2006 ዓ.ም

 

ዜና ቤተክርስቲያን ሐምሌና ነሐሴ 2006 ዓ.ም

zenaaugust14

የዜና ቤተክርስቲያን  ሐምሌና ነሐሴ 2006 ዓ.ም ለማንበብ ምስሉን ይጫኑ...

 

በዓለ ደብረ ታቦር

በዓለ ደብረ ታቦር

በዓለ ደብረ ታቦር

በብፁዕ አቡነ ገሪማ ፤
የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ ልዩ ጽ/ቤት
የውጭ ግንኙነት የበላይ ኃላፊ

 በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!

  • ‹‹ተፈሥሑ በእግዚአብሔር ዘረድአነ፤
  • ወየብቡ ለአምላከ ያዕቆብ፤
  • ንሥኡ መዝሙረ ወሀቡ ከበሮ፤
  • መዝሙር ሐዋዝ ዘምስለ መሰንቆ፤
  • ንፍሑ ቀርነ በዕለተ ሰርቅ፤
  • በእምርት ዕለት በዐልነ፤
  • እስመ ሥርዓቱ፤ ለእስራኤል ውእቱ››


በረዳታችን፣ በረድኤታችን በእግዚአብሔር ደስ ይበላችሁ፤ ለያዕቆብም አምላክ እልል በሉ፤ ዝማሬውን አንሡ፤ ከበሮውንም ስጡ ደስ የሚያሰኘውን በገና ከመሰንቆው ጋር በመባቻ ቀን በከፍተ...

ፍልሰታ ለማርያም ድንግል ወላዲተ አምላክ

"ፍልሰታ ለማርያም ድንግል ወላዲተ አምላክ"

በመምህር ሙሴ ኃይሉ (B.TH, MA in Philo)

የሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ምክትል ኃላፊ

ቅዱስ ጳውሎስ በሮሜ መልእክቱ "ወአመ በፅሐ ዕድሜሁ እግዚአብሔር ፈነወ ወልዶ ወተወልደ እምብእሲት፡- ነገር ግን የዘመኑ ፍጻሜ በደረሰ ጊዜ እግዚአብሔር ከሴት የተወለደውን ከሕግም በታች የተወለደውን ልጁን ላከ" /ገላ. 4፡4/ በማለት እንደገለጸልን ፍጠረኝ ሳይለው ከብዝሐ ፍቅሩ የተነሳ የፈጠረው የሰው ልጅ በፈጸመው ስሕተት ወይ በደል ተጸጽቶ፣ በዕንባና በለቅሶ ተሞልቶ፣ ማቅ ለብሶና አመድ ነስንሶ በንስሐ ሕይወት...

የፕሮቴስታንት እይታ ወጌሻ የሌለው የምላስ ወለምታ

የፕሮቴስታንት እይታ
ወጌሻ የሌለው የምላስ ወለምታ

ውድ አንባቢዎቻችን ከላይ ያስነበብኳችሁ ርዕስ በጥንቃቄ ካያችሁት ቀጥሎ ያለው ንባብ በትክክል ይገለጥላችኋል፡፡ ይህን ርዕስ የሰጠሁበትም ምክንያት ፕሮቴስታንት ወገኖቻችንን ለመንቀፍ ሳይሆን አመለካከታቸውን ወደ ትክክለኛው መስመር እንዲመልሱ ለማለት አስተያየት ለመስጠት ያህል ነው፡፡ መልካም ንባብ፤

የክርስቲያን ህብረት የሚባሉትን ሃይማኖተኞች ባጠቃላይ ወይም ክርስቶስን የሚያመልኩ ሃይማኖተኞችን ሁሉ አንድ የሚያደርጋቸው በጋራ የሚጠቀሙት መጽሐፍ ቅዱስ ነው፡፡ ይሁን እንጂ ከግማሽ በላይ የሚሆኑ ሃይማኖተኞች መ...

በኢትዮጵያ ሥልጣኔ የመንፈሳዊ ት/ቤቶች ሚና

በኢትዮጵያ ሥልጣኔ የመንፈሳዊ ት/ቤቶች ሚና

ንቡረ እድ ኤልያስ አብርሃ
የመንፈሳዊ ዘርፍ ምክትል ሥራ አስኪያጅ
በመምህራን ጉባኤ ወቅት ያቀረቡት ጥናታዊ ጽሑፍ

1. መግቢያ፤

የኢትዮጵያ ሥልጣኔና ታሪክ፣ ነጻነትና ጀግንነት፣ አንድነትና መልካም ሥነ ምግባር ዋና ምንጭ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ናት፤

በሌሎች ክፍለ ዓለማት እንዲህ ተሟልተው የማይገኙ እነዚህ አኲሪ ዕሴቶች የተፈጠሩትና ተጠብቀው የኖሩት በዐጸደ ቤተ ክርስቲያን በተስፋፉ ት/ቤቶች ነው፡፡

መቼም ዕውቀትና ሥልጣኔ የሚስፋፋው በትምህርት ቤት ውስጥ በሚሰጠው የመምህራን አስተምህሮ ነው፤ መ...

ትኩረት ለአብነት መምህራንና ለአብነት ት/ቤቶች በሚል የአብነት መምህራን ጉባኤ ዛሬ ተጀመረ፡፡

"ትኩረት ለአብነት መምህራንና ለአብነት ት/ቤቶች" በሚል የአብነት መምህራን ጉባኤ ዛሬ ተጀመረ፡፡

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/በት በትምህርትና ማሰልጠኛ መምሪያ አማካኝነት ለሁለት3 ቀናት የሚቆይ የምክክር ጉባኤ በጠቅላይ ቤተ ክህነት ስብከተ ወንጌል አዳራሽ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት፣ ብፁዕ አቡነ ማቴዎስ የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅና የወላይታ ኮንታ እና ዳውሮ አኅጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ...