መዝሙር (ግሩማን መላዕክት) February 16, 2020


 ግሩማን መላዕክት
 የምትተጉ ለምሕረት
 ኧኸ ለሠው ድህነት
 ከልዑል ዘንድ ለምኑልን
 ቸርነቱን እንዲያደርግልን/፪/

እስራኤልን በጉዞአቸው (2)
የመራሃቸው
ሚካኤል ነህ ጠባቂአቸው
ማዕበሉን ያሻገርካቸው

 ግሩማን መላዕክት
 የምትተጉ ለምሕረት
 ኧኸ ለሠው ድህነት
 ከልዑል ዘንድ ለምኑልን
 ቸርነቱን እንዲያደርግልን/፪/

ያበሰርካት ለድንግል (2)
ኧኸ የሕይወት ቃል
መልዕክተኛው ኧኸ ለልዑል
መልአከ ኃይል ገብርኤል

 ግሩማን መላዕክት
 የምትተጉ ለምሕረት
 ኧኸ ለሠው ድህነት
 ከልዑል ዘንድ ለምኑልን
 ቸርነቱን እንዲያደርግልን/፪/

እናቶችን በጭንቃቸው (2)
ኧኸ የምትረዳቸው
ሩፋኤል ነህ ጠባቂአቸው
በምጥ ጊዜ አዋላጃቸው

 ግሩማን መላዕክት
 የምትተጉ ለምሕረት
 ኧኸ ለሠው ድህነት
 ከልዑል ዘንድ ለምኑልን
 ቸርነቱን እንዲያደርግልን/፪/

ሡራፌል ወኪሩቤል
አፍኒን ወራጉኤል
ኧኸ ወሳቁኤል
በልዑል ፊት የምትቆሙ
ምልጃችሁን ሥለ እኛ አሰሙ