መዝሙር (ሰላም ለኪ) February 25, 2024 (First Mezmur)

✟ሰላም ለኪ✟
✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟
 ሰላም ለኪ እንዘ ንሰግድ ንብለኪ  ማርያም እምነ ናስተበቍአኪ  እምአርዌ ነአዊ ተማኅፀነ ብኪ በእንተ ሐና እምኪ ወኢያቄም አቡኪ ማኅበረነ ዮም (፫)ድንግል ባርኪ

መዝሙር (አንደበቴም ያዉጣ) February 18, 2024 (First Mezmur)

✟አንደበቴም ያዉጣ✟
✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟
ወጥመድ ተሰበረ እኔም አመለጥኩኝ
ከሃጢአት ፈላፃ ከሞት አተረፈኝ
የአናብስቱን አፍ በሀይሉ የዘጋ
የዳንኤል አምላክ ይኖራል ከኛጋ

 አንደበቴም ያዉጣ የምስጋና ቅኔ
 የአምላኬን ማዳን አይቻለሁ ባይኔ
 በገባኦን ሰማይ ፀሀይን ያቆመ
 ዛሬም ጎብኝቶኛል እየደጋገመ

አስፈሪዉ ነበልባል እሳቱ ቢነድም
ለጣኦት እንድንሰግድ ነገስታት ቢያዉጁም
ሁሉም ቢተወኚም ቢጠላኚም አለም
ፅናት ይሆነኛል ጌታ መድሀኒአለም
 አንደበቴም ያዉጣ የምስጋና ቅኔ
 የአምላኬን ማዳን አይቻለሁ ባይኔ
 በገባኦን ሰማይ ፀሀይን ያቆመ
 ዛሬም ጎብኝቶኛል እየደጋገመ

በዳዊት ምስጋና በያሬድ ዝማሬ
ከቅዱሳን ጋራ ልዘምር አብሬ
እርሱን ሳመሰግን ሚልኮን ብትስቅብኝ
ለጌታየ ክብር እዘምራለሁኝ

 አንደበቴም ያዉጣ የምስጋና ቅኔ
 የአምላኬን ማዳን አይቻለሁ ባይኔ
 በገባኦን ሰማይ ፀሀይን ያቆመ
 ዛሬም ጎብኝቶኛል እየደጋገመ