መዝሙር (የሰው ልጅ ሁልጊዜ) March 7, 2021 (First Mezmur)

የሰው ልጅ ሁልጊዜ በጣም ደስ ቢለው በጣም ደስ ቢለው /፪/
ደግሞ የጭንቁን ቀን ማሰብ ተገቢ ነው /፪/
ምንም ቢደሰቱ ቢበዛ ምቾት ቢበዛ ምቾት /፪/
አይቀርም በዃላ መወሰድ በሞት /፪/
ችግር ቢደራረብ ሃዘን ቢከበን ሃዘን ቢከበን /፪/
ከክርስቶስ ፍቅር ማንም አይለየን /፪/
ሳናውቀው ዲያቢሎስ እንዳይነጣጥለን እንዳይነጣጥለን /፪/
ነቅተን እንጠብቅ የእምነት ሰይፍን ይዘን /፪/

መዝሙር (ሰአሊ ለነ ቅድስት) February 28, 2021 (First Mezmur)


 ሰአሊ ለነ ቅድስት እንልሻለን/ ፪ /
 እንደ ኤፍሬም እንደ አባታችን
 ለምኝልን እመቤታችን / ፪ /

ተስፋቸው ነሽና ለፍጥረት ዓለም
እየተመኩብሽ እስከ ዘለዓለም
ኃጢአታቸው ተደምስሶላቸው
በአንቺ ጸሎት ዳነች ሕይወታቸው

 ሰአሊ ለነ ቅድስት እንልሻለን/ ፪ /
 እንደ ኤፍሬም እንደ አባታችን
 ለምኝልን እመቤታችን / ፪ /

ስምሽም ስልጡን ነው በእግዚአብሔር መንበር
ቃል ኪዳን ገባልሽ ዓለሙን ሊምር
በአንቺ ጸሎት ይተማመናሉ
ጠዋት ማታ ቅድስት ሆይ ይላሉ

መዝሙር (ከሰዎች ማነው) February 14, 2021 (Second Mezmur)

 ከሰዎች ማነው እንደ እኔ ትእዛዝህን ሻሪ/፪/
 ከአማልክትስ ማነው እንዳንተ መሐሪ /፪/

የኃጢአት ሸክም ከብዶብኝ ሲያስጨንቀኝ
ጠላቶች ከበው በእኔ ላይ ቢዝቱብኝ
ብቸኝነቴን አይተህ ስለደረስክልኝ
ተመስገን እንጂ ላንተ ሌላ ምን አለኝ

መዝሙር (ምን ሰማህ ዮሐንስ) February 7, 2021 (Second Mezmur)

 ምን ሰማህ ዮሐንስ በማኅጸን ሳለህ /፪/
 ሕፃን ሆነህ ነቢይ ለክብር የተጠራህ /፪/
 እንደ እንቦሳ ጥጃ ያዘለለህ ደስታ /፪/
 ምን አይነት ድምፅ ነው ምን አይነት ሰላምታ/፪/

ከተፈጥሮ በላይ ያሰገደህ ክብር
እንዴት ቢገባህ ነው የእናታችን ፍቅር /፪/
ሌላ ድምፅ አልሰማም ከእንግዲህ በኋላ
ለውጦኛልና የሰላምታ ቃሏ /፪/