መዝሙር (አንዲት ናት) February 16, 2020


 አንዲት ናት ቤተክርስቲያን አንዲት ናት(፪)
 ቋንቋና ዘር ቀለም ማይነጣጥሏት
 ክርስቶስ በደሙ የመሠረታት
 ቤተክርስቲያን አንዲት ናት

አዲስ አይደለንም ለመከራው ጉዞ
የወደቀ አናውቅም መስቀል ተመርኩዞ
አምላከ ቅዱሳን ከእኛ ጋር ነውና
በርቱ ክርስቲያኖች በእውነት ጎዳና(፪)

መዝሙር (ዮሐንስ መምህረ ትህትና) November 10, 2019


 ጥርጊያን ያዘጋጀህ ለአዲስ ኪዳን ፍኖት
 መምህረ ንሰሐ መጥምቀ መለኮት
 በምድር የተገለጥክ በኤልያስ መንፈስ
 ልጆችህን ባርከን /፫/ ካህኑ ዮሐንስ

ቀድሞ ያልነበረ ያልተጠራበት ሰው
ስምህን ከሰማይ ያወጣው አምላክ ነው
ነብየ ልዑል ሆይ በማኅፀን ሳለህ
የድንግል ሰላምታ በደስታ አዘለለህ