መዝሙር (ደጅ ጠናሁ) November 26, 2023 (Second Mezmur)

ደጅ ጠናሁ

==============
  ደጅ ጠናሁ ቆይቼ ኪዳነምህረትን
 ተፅናናሁኝ ረሳሁ ሀዘኔን
 የአምላክ እናት እመቤታችን
 ሞገስ ሁኚኝ ቀሪው ዘመኔን /2/
የመከራው ዘመን አለፈ እንደዋዛ
አንቺን ተጠግቼ የአለሟ ቤዛ
የልጅሽ ቸርነት ያንቺ ደግነት
ባሪያሽን ሰወረኝ ካስጨናቂ ሞት

  እናቴ ስምሽን ስጠራ
 አለፈ ያሁሉ መከራ
 እንባዬ ከፊትሽ ፈሰሰ
 እምዬ ባንቺ ነው የታበሰ
 ሰላም ለኪ!

 ደጅ ጠናሁ ቆይቼ ኪዳነምህረትን
 ተፅናናሁኝ ረሳሁ ሀዘኔን
 የአምላክ እናት እመቤታችን
 ሞገስ ሁኚኝ ቀሪው ዘመኔን /2/

መዝሙር (ሰዎች ደስ ይበለን) November 26, 2023 (First Mezmur)

ሰዎች ደስ ይበለን

==============
 ሰዎች ደስ ይበለን በአምላካችን
 ከኃጢአት ባርነት ነፃ ላወጣን
 ተነሱ እናመስግን ውለታው ብዙ ነው
 ምን ይከፈለዋል ተመስገን ብቻ ነው

በኃጢአት በሽታ ወድቄ ሳለሁኝ
መድሃኒት ክርስቶስ ከውድቀቴ አነሳኝ
ስጦታው ብዙ ነው ለኔ የሰጠኝ
ተመስገን ብቻ ነው አምላክ ላንተ ያለኝ

መዝሙር (አምላክ አትተወን) March 21, 2021

 አምላክ አትተወን የእጆችህ ሥራ ነን /፪/
 በየቀኑ ወደ አንተ እንጮሃለን
 ዝቅ ብለን እንለምንሃለን

ቀድሞ አባቶቻችን በአንተ ስለ አመኑ /፪/
ታድናቸው ነበር ቆመው ሲለምኑ /፪/

 አምላክ አትተወን የእጆችህ ሥራ ነን /፪/
 በየቀኑ ወደ አንተ እንጮሃለን
 ዝቅ ብለን እንለምንሃለን

መዝሙር (ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ) March 14, 2021

ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ እግዚአብሔር
ለአማልክት አምላክ እናቅርብለት ምስጋና
ምህረቱ ለዘላለም ነውና
ለነገሥታት ንጉሥ እናቅርብለት ምስጋና
የእስራኤል አምላክ ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ
በጠራንህ ጊዜ ፈጥነህ ድረስ /፫/

 ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ እግዚአብሔር
 ተገዙ ለእግዚአብሔር ስሙንም ጥሩ
 ድንቅ ሥራውንም ለአሕዛብ ንገሩ
 የእስራኤል አምላክ ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ
 በጠራንህ ጊዜ ፈጥነህ ድረስ/፫/