መዝሙር (ለዚህ ላደረሰን) October 6, 2019



 ለዚህ ላደረሰን በሰላም በጤና /፪/
 ሃሌ ሃሌ ሉያ /፪/ እናቅርብ ምሥጋና

ሥራችንን ዐይቶ በደላችንን
ይህን ሁሉ ታግሦ ለዚህ ላበቃን
 ሃሌ ሃሌ ሉያ /፪/ እናቅርብ ምሥጋና

አንተ በምሕረትህ ለዚህ ላደረስከን
የአንድ ቀንም ዕድሜ ስለጨመርክልን
ቸሩ አምላካችን ሆይ አንተን እናመሥግን
 ሃሌ ሃሌ ሉያ /፪/ እናቅርብ ምሥጋና

ጌታ አምላካችን ሆይ ተስፋችን አንተው ነህ
እምነታችን ይጽና ፈቃድህ ይሁንልን
አንተ በምሕረትህ በይቅርታህ ጎብኘን
 ሃሌ ሃሌ ሉያ /፪/ እናቅርብ ምሥጋና

 ለዚህ ላደረሰን በሰላም በጤና /፪/
 ሃሌ ሃሌ ሉያ /፪/ እናቅርብ ምሥጋና

መዝሙር (ምስጉን ነው የተመሰገነ) September 22, 2019



 ምስጉን ነው የተመሰገነ
 ባሪያውን እኔን ይቅር ያለ
 ይመስገን ይመስገንልኝ
 ጎጆዬን አምላክ ሞላልኝ

እጅህ ሰፊ እንደሆነ አውቃለሁ ጌታዬ
የጎደለው ሞልቷል ይድረስ ምስጋናዬ
ያጣሁትን ካንተ አጎኝቻለሁ
ሁሉን ነገር ለበጎ ብያለሁ

 ምስጉን ነው የተመሰገነ
 ባሪያውን እኔን ይቅር ያለ
 ይመስገን ይመስገንልኝ
 ጎጆዬን አምላክ ሞላልኝ

ማቄን የቀደደው ተስፋን ያስታጠቀኝ
ባዶ የነበርኩት ሁሉን ተሰጠኝ
ሰጪም ነሺም እግዚአብሔር ብቻ ነው
የሰው ድርሻ በር ማንኯኯት ነው

 ምስጉን ነው የተመሰገነ
 ባሪያውን እኔን ይቅር ያለ
 ይመስገን ይመስገንልኝ
 ጎጆዬን አምላክ ሞላልኝ

እገፋለሁ እንጂ እኔ አልጨነቅም
መሰረቴ አንተ ነህ ከቶ አልናወጥም
የተሰጠኝ የሚታየውን
እንዳትነሳኝ የዘላለሙን

 ምስጉን ነው የተመሰገነ
 ባሪያውን እኔን ይቅር ያለ
 ይመስገን ይመስገንልኝ
 ጎጆዬን አምላክ ሞላልኝ

ቢሰጥ አያልቅበት ለካስ ክቡር ጌታ
ሁሉን የከወነ በልዩ ስጦታ
ድሆች ስንሆን ሁሉን አለንና
አምላካችን ይድረሰው ምስጋና

 ምስጉን ነው የተመሰገነ
 ባሪያውን እኔን ይቅር ያለ
 ይመስገን ይመስገንልኝ
 ጎጆዬን አምላክ ሞላልኝ

መዝሙር (ደጅ ጠናሁ) June 9, 2019



 ደጅ ጠናሁ ቆይቼ ኪዳነምህረትን
 ተፅናናሁኝ ረሳሁ ሀዘኔን
 የአምላክ እናት እመቤታችን
 ሞገስ ሁኚኝ ቀሪው ዘመኔን (፪)

የመከራው ዘመን አለፈ እንደዋዛ
አንቺን ተጠግቼ የአለሟ ቤዛ
የልጅሽ ቸርነት ያንቺ ደግነት
ባሪያሽን ሰወረኝ ካስጨናቂ ሞት
እናቴ ስምሽን ስጠራ
አለፈ ያሁሉ መከራ
እንባዬ በፊትሽ ፈሰሰ
እምዬ ባንቺ ነው የታበሰ
ሰላም ለኪ

መዝሙር (ያከብርዋ ለሰንበት) June 2, 2019



ያከብርዋ ለሰንበት መላእክት በሰማያት ጻድቃን በውስተ ገነት፤ (2)
ወኩሉ ፍጥረት አሳት ወአናብርት እለ ውስተ ደይን ያእርፉ ባቲ እስመ ባቲ ኣእረፈ እምኩሉ ግብሩ፤/2/

ያከብሯታል ሰንበትን መላእክት ጻድቃን በገነ/2/
ፍጥረታት በሙሉ አሳዎችና አንባሪዎች በመቃብር ያሉ ያከብሯታል አምላክ በርሷ ስለ አረፈ ከስራው ሁሉ፤ /2/