ወረብ December 1, 2023


እንዘ ዘልፈ ትነብር ውስተ ቤተ እግዚአብሔር።
አስተርአያ መልአክ ዘኢኮነ ዘኢኮነ ከመ ቀዲሙ ኢኮነ።

ትርጉም
ዘወትር በእግዚአብሔር ቤት ውስጥ ተቀምጣ ሳለ
እንደ ቀድሞ ያልሆነ መልአክ ታያት፡፡

መዝሙር (በማህፀን ቅኔ) December 10, 2023 (Second Mezmur)

በማህፀን ቅኔ

==============
 በማህፀን ቅኔ ለማርያም ተሰማ
 በተራራማ ሃገር በኤፍሬም ከተማ
 ዩሐንስ ይናገር በረሃ ያደገው
 ድንግል ስትናገር ምን እንዳዘለለው /2/

የእናቱ ማህፀን የቅኔ ርስት ሆነች
ድንግል የአምላክ እናት ፊቱ ስለቆመች
በሃሴት ዘለለ ዘመረ በደስታ
ከድንግል ሲወጣ ታላቁ ሰላምታ

መዝሙር (የሰው ልጆች ሁላችን እንማር) December 10, 2023 (First Mezmur)

የሰው ልጆች ሁላችን እንማር

==============
 የሰው ልጆች ሁላችን እንማር
 አስተባብረን ሃይማኖት ከምግባር
 የሰው ልጆች ሁላችን እንማር
 መልካም ሥራን በመሥራት እንኑር

የሰይጣን ድል መንሻ የክብር መውረሻ
ሃይማኖት ናትና እውነተኛ ጋሻ

 የሰው ልጆች ሁላችን እንማር
 አስተባብረን ሃይማኖት ከምግባር
 የሰው ልጆች ሁላችን እንማር
 መልካም ሥራን በመሥራት እንኑር

ለእውነትኛ ስራ ሁላችን እንበርታ
ጻድቃን ሰማዕታትን አድርገን መከታ

 የሰው ልጆች ሁላችን እንማር
 አስተባብረን ሃይማኖት ከምግባር
 የሰው ልጆች ሁላችን እንማር
 መልካም ሥራን በመሥራት እንኑር

ፍዳ ዓለምን አልፈን እንድንሄድ ሁላችን
ጸንተን መገኘት ነው በሃይማኖት

 የሰው ልጆች ሁላችን እንማር
 አስተባብረን ሃይማኖት ከምግባር
 የሰው ልጆች ሁላችን እንማር
 መልካም ሥራን በመሥራት እንኑር

የሰይጣን ድል መንሻ የክብር መውረሻ
ሃይማኖት ናትና እውነተኛ ጋሻ

 የሰው ልጆች ሁላችን እንማር
 አስተባብረን ሃይማኖት ከምግባር
 የሰው ልጆች ሁላችን እንማር
 መልካም ሥራን በመሥራት እንኑር

እምነታችን ሁሉ ይሁን በፈጣሪ ይቅር ባይ ነውና የእኛ አምላክ መሃሪ  የሰው ልጆች ሁላችን እንማር
 አስተባብረን ሃይማኖት ከምግባር
 የሰው ልጆች ሁላችን እንማር
 መልካም ሥራን በመሥራት እንኑር

መዝሙር (እልል በሉ) December 3, 2023 (First Mezmur)

እልል በሉ

==============
 እልል በሉ በአንድነት ዘምሩ
 አመስግኑ ለክብሩ ዘምሩለት
 እንደ እግዚአብሔር ያለ ማንም የለም በሉ

በኃጢያት ባርነት ስንኖር ተገዝተን
ከቤቱ ስንርቅ ትእዛዙን አፍርሰን
አይቶ ዝም ላላለን ጠላቶቹ ስንሆን
ውለታው ብዙ ነው ክብር ለዕርሱ ይሁን/2/