፩-  ስድስተኛው የኢትዮጵያ ቅዱስ ፓትርያርክ (አቡነ ማቲያስ)

፪-  ካህኑ የመጥምቀ መለኮት አባት (ዘካርያስ)

፫-  የነቢዩ ኤልያስ ደቀ መዝሙር (ነቢዩ ኤልሳዕ)

፬-  በቃና ዘገሊላ ያማለደችው እናት (ቅድስት ድንግል ማርያም)

፭-  የቅዱስ ጳውሎስ ስም በጌታችን ከመጠራቱ በፊት (ሳውል)

፮-  በመምሬ አድባር ዛፍ ሥር እግዚአብሔር የተገለጠለት

    (አብርሃም)

፯-  ስምንተኛው የዐቢይ ጾም ሳምንት (ሆሣዕና)

፰-  እግዚአብሔርን ከፍ ባለ ዙፋን ላይ ተቀምጦ ያየው ነቢይ

     (ነቢዩ ኢሳይያስ)

፱-  ጌታችን ከበለስ ዛፍ ሥር አየሁህ ያለው (ናትናኤል)

፲-  በካህኑ ዔሊ ፊት ሲያገለግል የነበረው ብላቴና (ካህኑ ዔሊ)

፲፩- ጌታችን በዲያብሎስ የተፈተነበት ገዳም (ገዳመ ቆሮንቶስ)

፲፪- የጌታዬ እናት ወደኔ ትመጣ ዘንድ እንዴት ይሆናል ያለች

     (ቅድስት ኤልሳቤጥ)

፲፫- እግዚአብሔር ከሚጠላቸው ፮ ነገሮች አንዱ (መጽ.ምሳሌ)

     (ትዕቢተኛ ዓይን)

፲፬- የቅዱስ ጴጥሮስ የቀደመ ስሙ (ስምዖን)

፲፭- በሙሴ እግር የተተካው (ነቢዩ ኢያሱ)