የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ ጤናማ ክብደትን ከመጠበቅ ባሻገር የኮለስትሮልንና የደም ግፊትን መጠን ለመቀነስ ያስችላል። እድሜያቸው ከአሥራ ስምንት ዓመት በላይ ያሉ ጎልማሶች በሳምንት ውስጥ ባሉት አብዛኛው ቀናት ከግማሽ ሰዓት ያላነሰ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ እንደሚገባቸው ዩናይትድ ስቴትስ ዋና የጤና ጥበቃ ማእከል ያዛል።

መደበኛና ተከታታይ የሆነ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ ለጤናዎ መጠበቅ ከሚያደርጉዋቸው ነገሮች ሁሉ በዋነኛነት ሊከተታተሉት የሚገባ ነው።

  •           የአካል​​ ​​ብቃት​​ ​​እንቅስቃሴ ዋና ዋና ጥቅሞች፦
  •           ክብደትዎን ለመቆጣጠር
  •          በልብ በሽታ የመታመም እድልዎን ለመቀነስ

የሁለተኛው ዓይነት የስኳር በሽታና ተዛማች የሆኑ የጤና እክሎችን ለመቀነስ በጥቅል ስሙ metabolic syndrome የሚባለውን ዘርፈ ብዙ የጤና ቀውስ እድል ለመቀነስ ይረዳናል፤ ይኼውም በሆድና ዳሌ ላይ የሚከማች ስብን፤ ከፍተኛ የደም ግፊትን ፤ከፍተኛ የደም ስኳር መጠንና በደም ውስጥ ያሉ ስብ ነክ ንጥረ ነገሮችን (triglycerides) ለመቀነስ) እና ጥሩ የሚባለውን ኮሎስተሮል ዓይነት ለመጨመር ይረዳናል።

  •          በአንዳንድ የካንሰር ዓይነቶች የመታመም እድልዎን ለመቀነስ
  •          አጥንትዎንና ጡንቻዎን ለማጠንከር
  •         የአእምሮ ጤናዎን ለማሻሻል
  •         ረጅም እድሜ ለመኖር ያልዎትን እድል ለመጨመር

 

የአካል ብቃት እንቅስቃሴዎን ለመጨመርና ጤናዎን ለማሻሻል በቅድስት ሥላሴ የአምስት ሺህ ርምጃና ሩጫ ላይ ለመሳተፍ ይዘጋጁ። ትኬት በድረ ገጽ ላይ መግዛት ይችላሉ፡፡ www.minnesotaselassie.org/5k

 

በተጨማሪም ቅዳሜ ጠዋት በሚደረገው የእግር ኳስ ልምምድ ላይ እርስዎና ቤተሰብዎ ይሳተፉ።

 

          አድራሻ፡ Pearl Park, Portland Ave. and E 53rd S — close to 5288 Portland Ave S, Minneapolis, MN

 

በአንድነት ተሰባስበው የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ላይ ለመሳተፍ ባይችሉ እንኳ ከማኅበረሰብዎ ጋር እርስ በራስ ለመበረታታትና ለመወዳደር ብሎም እንቅስቃሴዎን ለመጨመር የጤና ክፍላችን ባዘጋጀው ድረ ገጽ ላይ ተመዝግበው የአካል ብቃት እንቅስቃሴዎን ይጨምሩ። https://app.inkin.com/group/631/contest/list

ለተጨማሪ መረጃ የሚከተለውን ድረ ገጽ ይመልከቱ፦ (Physical Activity and Health) https://www.cdc.gov/physicalactivity/basics/pa-health/index.htm

 

 

 

  is sponsoring it’s first Health Village, to be hosted at the Kidist Selassie 5K on July 29, at Phalen Park. Free health screenings and health education booths. Please stop by each booth. Health screening participants will receive incentives.

 

 

 

 

ይስሐቅ ቱራ (RN)

የምእመናን የጤና አገልግሎት ክፍል

Faith Community Health Program