ወንጌላዊው ዮሐንስ በመልእክቱ ሕይወትም ተገለጠ አይተንማል እንመሰክርማለን፥ ከአብ ዘንድ የነበረውንም ለእኛም የተገለጠውን የዘላለምን ሕይወት እናወራላችኋለን። (፩ዮሐ. ፩፡፪) በማለት እንዳስተማረን አባቶቻችን ሐዋርያት ከኢየሱስ ክርስቶስ ያገኙትን ቀጥተኛና ትክክለኛ ትምህርት በወንጌል ጽፈው፣ በስብከት አስተምረው እና በመልእክታቸው አስተላልፈው አሁን ባለንበት ዘመን እንዲደርስ እንዳደረጉት እኛም የጌታችንን እና የአባቶቻችንን አስተምህሮ አበው እንዳስተማሩት "ጽርሐ አርያም" በተሰኘችው ወርኻዊ ጋዜጣችን ላይ  ስናወጣ ከፍተኛ ደስታ ይሰማናል። አንባብያን በቤተ ክርስቲያናችን ድረ-ገጽ ላይ በመግባት ትምህርቶችን፣ አገልግሎቶችን፣ ቤተሰባዊ መልእክቶችን እና ጠቃሚ መረጃዎችን እንድትከታተሉ እናሳስባለን።