መዝሙር (አቤት የዚያን ጊዜ) March 31, 2019



 አቤት የዚያን ጊዜ ክርስቶስ ሲመጣ /፪/
 ትንሹም ትልቁም /፫/ መድረሻውን ሲያጣ

ከምሥራቅ ከምዕራብ ከሰሜን ከደቡብ /፪/
ነፋሳት ሲላኩ /3/ መዓትን ለማዝነብ
ሰማይና ምድር በአንድ ሲዋሐዱ /፪/
የት ይሆን መድረሻው /፫/ የት ይሆን መንገዱ

መዝሙር (አድኚኝ እናቴ) March 24, 2019



 አድኚኝ እናቴ ከሥጋ ፈተና
 ሥጋዬ ከኃጢአት ከቶ አልራቀምና
 ሸክሜ የከበደኝ ብቸኛ ሆኛለሁ
 አትለይኝ ድንግል አደራ እልሻለሁ /፪/

የአማኑኤል እናት የተዋሕዶ አክሊል
አትጥፊ ከመሃል እንድትሆኚን ኃይል
ምንም ቢበዛብሽ የእኛ ጉስቊልና
ከእኛ ጋራ ከሆንሽ አለን ቅድስና /፪/