መዝሙር (ትምክሕተ ዘመድነ) December 23, 2018

 ትምክሕተ ዘመድነ /፪/ ማርያም እምነ
 ማርያም ትምክሕተ ዘመድነ

የድኅነታችን ዓርማ የነፃነታችን
የሕይወት መሠረት ነሽ ድንግል እናታችን
አንቺን ለእኛ ዘርን ባያስቀር
እንደ ጥንቱ እንደ ሰዶም ምድር
ሁላችን በጠፋን ነበር

መዝሙር (ሠርዓ ለነ) December 16, 2018

 ሠርዓ ለነ ሰንበተ ለእረፍተዚአ (፪)
 ሠርዓለነ ሰንበተ ለእረፍተዚአ ኧኸ ሠርዓለነ ሰንበተ ለእረፍተዚአ
 ሠራልን ሰንበትን ለእረፍታችን (፪)
 ሠራልን ሰንበትን ለእረፍታችን ኧኸ ሠራልን ሰነበትን ለእረፍታችን

በስድስቱ ቀናት ሁሉን ነገር ሰርቶ
ሰባተኛው ቀን ለእረፍት አዘጋጅቶ
ለሁላችን ሰጠን ከቀናት ለይቶ
 ሠርዓ ለነ ሰንበተ ለእረፍተዚአ ኧኸ ሠርዓለነ ሰንበተ ለእረፍተዚአ

መዝሙር (ዘየአምር) December 9, 2018 (Second Mezmur)


ዘየአምር እምቅድመ ኅሊና ዘይሄሊ ልበ የአምር (፪)
አርዓየ ኃይሎ በላእሌነ ወጸገወነ ኧኸ ሰናይቶ እግዚአብሔር (፪)

 ትርጉም ፦ልብ ያሰበውን ከህሊና አስቀድሞ ያውቃል
 እግዚአብሔር ኃይሉን በላያችን አሳይቶ መልካሙን ሰጠን

መዝሙር (ምን ሰማህ ዮሐንስ) December 9, 2018


 ምን ሰማህ ዮሐንስ በማህጸን ሳለህ (፪)
 ህፃን ሆነህ ነቢይ ለክብር የተጠራህ (፪)
 እንደ እንቦሳ ጥጃ ያዘለለህ ደስታ (፪)
 ምን አይነት ድምፅ ነው ምን አይነት ሰላምታ (፪)

ከተፈጥሮ በላይ ያሰገደህ ክብር
እንዴት ቢገባህ ነው የእናታችን ፍቅር (፪)
ሌላ ድምፅ አልሰማም ከእንግዲህ በኋላ
ለውጦኛልና የሰላምታ ቃሏ (፪)