መዝሙር (ምስጉን ነው የተመሰገነ) May 23, 2019



 ምስጉን ነው የተመሰገነ
 ባሪያውን እኔን ይቅር ያለ
 ይመስገን ይመስገንልኝ
 ጎጆዬን አምላክ ሞላልኝ

እጅህ ሰፊ እንደሆነ አውቃለሁ ጌታዬ
የጎደለው ሞልቷል ይድረስ ምስጋናዬ
ያጣሁትን ካንተ አጎኝቻለሁ
ሁሉን ነገር ለበጎ ብያለሁ

 ምስጉን ነው የተመሰገነ
 ባሪያውን እኔን ይቅር ያለ
 ይመስገን ይመስገንልኝ
 ጎጆዬን አምላክ ሞላልኝ

ማቄን የቀደደው ተስፋን ያስታጠቀኝ
ባዶ የነበርኩት ሁሉን ተሰጠኝ
ሰጪም ነሺም እግዚአብሔር ብቻ ነው
የሰው ድርሻ በር ማንኯኯት ነው

 ምስጉን ነው የተመሰገነ
 ባሪያውን እኔን ይቅር ያለ
 ይመስገን ይመስገንልኝ
 ጎጆዬን አምላክ ሞላልኝ

እገፋለሁ እንጂ እኔ አልጨነቅም
መሰረቴ አንተ ነህ ከቶ አልናወጥም
የተሰጠኝ የሚታየውን
እንዳትነሳኝ የዘላለሙን

 ምስጉን ነው የተመሰገነ
 ባሪያውን እኔን ይቅር ያለ
 ይመስገን ይመስገንልኝ
 ጎጆዬን አምላክ ሞላልኝ

ቢሰጥ አያልቅበት ለካስ ክቡር ጌታ
ሁሉን የከወነ በልዩ ስጦታ
ድሆች ስንሆን ሁሉን አለንና
አምላካችን ይድረሰው ምስጋና

 ምስጉን ነው የተመሰገነ
 ባሪያውን እኔን ይቅር ያለ
 ይመስገን ይመስገንልኝ
 ጎጆዬን አምላክ ሞላልኝ

መዝሙር (አታውኪኝ ነፍሴ) April 14, 2019



አታውኪኝ ነፍሴ አታስጨንቂኝ /፪/
በዓለም መድኃኒት በእግዚአብሔርታመኝ

ዋልያ እንደሚናፍቅ ወደ ውኃ ምንጮች
አቤቱ ወደ አንተ ነፍሴ ናፈቀች

መቼ ተነሥቼ መቼ እደርሳለሁ
የአምላኬንስ ፊቱን መቼ አየዋለሁ

የሕይወትን ውኃ እያስታወሰች
ነፍሴ ወደ ሕያው አምላክ ተጠማች

አታውኪኝ ነፍሴ አታስጨንቂኝ /፪/
በዓለም መድኃኒት በእግዚአብሔር ታመኝ