መዝሙር (ገሊላ እተዊ) November 11, 2018

እመቤቴ እስከ መቼ በባዕድ ሀገር ትኖሪያለሽ /፪/
ገሊላ ግቢ /፬/ አገርሽ ገሊላ ግቢ
ገሊላ እትዊ /፬/ ሀገረኪ ገሊላ እትዊ (፪)

እመቤቴ ማርያም ገሊላ እትዊ ስደቱ ይበቃሻል ገሊላ እትዊ
ሔሮድስ ሞቷል ብሎ ገሊላ እትዊ ገብርኤል ነግሮሻል ገሊላ እትዊ
በእሳት ሰረገላ ገሊላ እትዊ ዑራኤል ይመራሻል ገሊላ እትዊ
ሃገረኪ ገሊላ እትዊ ሃገረኪ ገሊላ እተዊ/፪/

መዝሙር (ተመለሺ ሱላማጢስ ተመለሺ) October 28, 2018


 ተመለሺ ሱላማጢስ ተመለሺ እናይሽ ዘንድ ተመለሺ
 የአባትሽን ቤት አትርሺ
 ተመለሺ ሱላማጢስ እመቤቴ ተመለሺ
 የአባትሽን ቤት አትርሺ

መኃ ፯ ፧ ፩
ኢሳይያስ ተንብዮልሽ
ፈጣን ደመና ያለሽ
ጌታን በጀርባሽ አዝለሽ
በግብፅ በረሃ የዞርሽ
የበረሃው ሙቀት ንዳድ
የሌሊቱ ግርማ ከባድ
በአራዊቱ ድምፅ ሁካታ
ልብሽ በጭንቅ ሲንገላታ

መዝሙር (አዳምን ለማዳን) October 21, 2018


 ሰአሊ ለነ ማርያም
አዳምን ለማዳን ሰው የሆነው ወዶ
ስደትን ጀመረ በፍቅር ተዋርዶ
 ሰአሊ ለነ ማርያም
ብርድ በጸናበት በክረምት ወራት
ልጅሽን ታቅፈሽ ተነሳሽ ስደት
 ሰአሊ ለነ ማርያም
የሄሮድስ ጭፍሮች ከሐገር ሲያሳድዱሽ
ልጅሽን ታቅፈሽ እንባሽን አፈሰስሽ
 ሰአሊ ለነ ማርያም
ለምኝልን ማርያም ከአንድዬ ከልጅሽ ከመድኃኔ ዓለም
አንቺ ብቻ እኮ ነሽ ለእግዚአብሔር ፍጹም
 ሰአሊ ለነ ማርያም
ሰሎሜና ዮሴፍን ዘመድ ኣግኝተሽ
ልጅሽን ታቅፈሽ ስደትን ጀመርሽ
 ሰአሊ ለነ ማርያም
ፍጡራን በሙሉ ከቤታቸው ሆነው
አንቺ መሰደድሽ ኧረ ለምንድን ነው
 ሰአሊ ለነ ማርያም
ከረሃብ ጋር ጸሐይ አንዴት አረገሽ
ሀዘንሽን ልካፈል ስለሆንኩ ልጅሽ
 ሰአሊ ለነ ማርያም
አንድ ፍሬ ሕጻን ትንሽ ብላቴና
እንዴት አቋረጥሽው በረሃውን ሲና
 ሰአሊ ለነ ማርያም
ምን አለች ኮቲባ ያልታደለች ፍጡር ጌታዋን ታቅፈሽ ስትዞሪ መንደር  ሰአሊ ለነ ማርያም
አንቺን የመሰለች አንዲህ መቸገሩ ብሆትኚ ነው ክፉ ያዞረሽ ባገሩ  ሰአሊ ለነ ማርያም
ብላ ተናገረች ምስጢሩ ሳይገባት ውሃን ለመዘከር ልቧ ጨክኖባት  ሰአሊ ለነ ማርያም
ክፉም አልመለስሽ እንባሽን አፈሰስሽ ለውሻ እራርተሽ ውሃን የተዘከርሽ  ሰአሊ ለነ ማርያም
ድንገት ወንበዴዎች ደርሰው ሲይዙሽ ከሰሎሜ ወስደሽ ልጅሽን ታቀፍሽ  ሰአሊ ለነ ማርያም
የሌሊት ቁርና የቀን ሀሩርን የተቀበልኩብህ ላላድን ነውን  ሰአሊ ለነ ማርያም
እያልሽ አለቀስሽ ምርር ብለሽ ፊቱ ላይ ወረደ የሐዘን እንባሽ  ሰአሊ ለነ ማርያም
ልጄን ሲገድሉብኝ ከማይ በህይወቴ እኔን ያስቀድመኝ ይቅረብልኝ ሞቴ  ሰአሊ ለነ ማርያም
ያበሰረኝ መልአክ ትወልጂያለሽ ያለኝ ዛሬ በስደቴ ይምጣና ያጽጽናናኝ  ሰአሊ ለነ ማርያም
ብለሽ ማልቀስሽን ባስታወስኩኝ ጊዜ ልቤ ይቃጠላል በሀዘን በትካዜ  ሰአሊ ለነ ማርያም
ከዘመድ መለየት ከሀገር መውጣት እንዴት ያሳዝናል የድንግል ስደት  ሰአሊ ለነ ማርያም
እንባሽ የወረደው አንደ ሐምሌ ደመና ሐዘንሽ ልዩ ነው የእስራኤል መና  ሰአሊ ለነ ማርያም
ጥቂት እፎይ ያልሽው ያኔ በስደትሽ ኢትዮጵያ ስትደርሺ ነበር የተጽናናሽ  ሰአሊ ለነ ማርያም
እንግዲህ አሳስቢ ድንግል ስደትሽን የደረሰብሽን ረሃብ ጥምሽን  ሰአሊ ለነ ማርያም
ስደትሽን ላስብ ስደተኛ ነኝ የሰማዩ ቤቴ የሚናፍቀኝ  ሰአሊ ለነ ማርያም
ነይ ነይ ነይ በረድኤት በአማላጅነትሽ ይሰጠን ምህረት  ሰአሊ ለነ ማርያም
በይ በእናትነትሽ አመሌን ቻይው ትኅትና እንደሆን ከተፈጥሮሽ ነው