መዝሙር (ድንግል ሆይ ስለ አንቺ) March 10, 2019



 ድንግል ሆይ ስለ አንቺ ነውና መሐሪ
 አማልጂኝ ከአንድ ልጅሽ ከፈጣሪ

ስሙን እንዳልጠራ አንደበትም የለኝ
ፊቱንም እንዳላይ ሥራዬ አስቸገረኝ

 ድንግል ሆይ ስለ አንቺ ነውና መሐሪ
 አማልጂኝ ከአንድ ልጅሽ ከፈጣሪ

ታውቆኛል ጥፋቴ ብዙ እንደበደልኩኝ
ትእዛዙን እንደሻርኩ ህጉን እንደጣስኩኝ

 ድንግል ሆይ ስለ አንቺ ነውና መሐሪ
 አማልጂኝ ከአንድ ልጅሽ ከፈጣሪ

በፊቱ እንዳላፍር የተጠራሁ ለታ
እለምነዋለሁ ከአሁኑ ይቅርታ

 ድንግል ሆይ ስለ አንቺ ነውና መሐሪ
 አማልጂኝ ከአንድ ልጅሽ ከፈጣሪ

አንተ ክቡር መልአክ ልደቱን አብሣሪ
አማልደኝ ከጌታዬ ከፈጣሪ

 ድንግል ሆይ ስለ አንቺ ነውና መሐሪ
 አማልጂኝ ከአንድ ልጅሽ ከፈጣሪ

ፃድቃን ሰማእታት እናንተም ሁላችሁ
አማልዱኝ ከአምላኬ ከአምላካችሁ

 ድንግል ሆይ ስለ አንቺ ነውና መሐሪ
 አማልጂኝ ከአንድ ልጅሽ ከፈጣሪ

መዝሙር (አማን በአማን) March 10, 2019

 አማን በአማን /፬/
 አማኑኤል ተመስገን ለዚህ ፍቅርህ ምን እንበል /፪/

ድብቁን ኃጢአት አንተ ብትገልጸው
ይቅር ብለኸኝ ባትሸፋፍነው
እንደ ሰው በቀል ቢኖርህ ጌታ
ለእኔ ኃጢአትስ የለውም ቦታ

 አማኑኤል ተመስገን ለዚህ ፍቅርህ ምን እንበል /፪/

መዝሙር (እግዚአብሔር ሆይ እወድሃለሁ) March 3, 2019



 እግዚአብሔር ሆይ እወድሃለሁ
 ስለ ስምህ እቃጠላለው
 ፍቅርህ እኔን ይመስጠኛል
 እንደ እግዝአብሔር ከየት ይገኛል(፪)

አለም ሁሉ በጠላኝ ጊዜ
ስንገላታ ይዞኝ ትካዜ
አንተ ከኔ አልተለየህም
እግዝአብሔር ሆይ ወደር የለህም (፪)

መዝሙር (አድነነ እግዚኦ) February 17, 2019

አድነነ እግዚኦ አድነነ አምላክነ /2×
ዘአዳንካ ለነነዌ ሃገር በትንብልና ትንብልና ሳዕልከ /2×

ትርጉም
አድነን ጌታ ሆይ አድነን አምላካችን /2×
ያዳንካት የነነዌን ሃገር በይቅርታ ባአምላካዊ ይቅርታ /2×