መዝሙር (ያዋጅ ነጋሪ ቃል) September 16, 2018


 የደናግል መመኪያ የነቢያት ገዳም
 አውደ ዓመቱን ባርኪልኝ ድንግል ማርያም

ያዋጅ ነጋሪ ቃል በበረሃ አየለ
የእግዚአብሔርን መንገድ አስተካክሉ እያለ
ምስክርነቱን ዮሐንስ ካስረዳን
ልባችን ለጌታ መልካም መንገድ ይሁን

መዝሙር (መላእክት በሰማያት) August 26, 2018


መላእክት በሰማያት እኅትነ ይብልዋ ሰማዕት ይኤምእዋ(፪)
ጻድቃን ይቄድስዋ በበነገዶሙ ይዌድስዋ (፪)
መላእክት በሰማያት እኅታችን ይሏታል ሰማዕታትም እጅ ይነሷታል(፪)
ጻድቃን ያመሰግኗታል በየነገዳቸው ያወድሷታል (፪)

መዝሙር (አምላካችን ተመስገን) August 5, 2018


 አምላካችን ተመስገን /፪/ ለዚህ ቀን ያደረስከን
 አምላካችን ተመስገን /፪/ ለዛሬ ያደረስከን

የሕይወትን መዝገብ ቃሉን ያስነበቡህ
በኃጢአት ስንማቅቅ በምሕረትህ ጠራኸን
በዓለም ስንባዝን ነበር በይቅርታህ መራኸን
አምላክ ሆይ ተመስገን
ትዕግሥትህ ብዙ ነው አያልቅም ርኅራኄህ
የምንከፍልህ ምን ይሆን ብዙ ነው ውለታህ
አምላክ ሆይ ተመስገን

መዝሙር (እሰይ ተወለደ) July 8, 2018

እሰይ ተወለደ በዛሬዋ እለት
መጥምቁ ዮሃንስ ታላቁ ሰማዕት

የምሥራች እልል በሉ የአዳም ልጆች ሁሉ
የምሥራች እልል በሉ ክርስቲያኖች ሁሉ