መዝሙር (የአርባብ አለቃ) July 29, 2018

 የአርባብ አለቃ ቅዱስ ገብርኤል  አብሣሬ ትስብእቱ ለቀዳሜ ቃል  ምሕረት አሰጠን ከአምላክ ከልዑል
በሦስቱ ሰማያት በመላእክት ከተማ
ሳጥናኤል ተነሥቶ ክህደትን ሲያሰማ
ጽኑ ብለህ ያቆምህ መላእክትን በእምነት
እኛንም አድነን አጽናን በሃይማኖት

መዝሙር (በለኒ መሐርኩከ) July 1, 2018


በለኒ መሐርኩከ በለኒ መሐርኩኪ በእንተ ማርያም (፪)
እስመ አልቦ ዘእንበሌከ ዘይሜህር ቃለ መድኃኔ ዓለም (፪)

በለኝ ምሬሃለው በለኝ ምሬሻለሁ ስለማርያም (፪)
የለምና የሚምር ቃል ያለ አንተ መድኃኔ ዓለም (፪)

መዝሙር (ተክለሃይማኖት ተክለ አብ) July 1, 2018


 ተክለሃይማኖት ተክለ አብ ተክለ ወልድ ተክለ መንፈስ ቅዱስ
 አባታችን አማልደን አስታርቀን ከፈጣሪ ጋር ከአምላካችን

በሦስት ቀን ሥላሴን ያመሰገንህ
ከጭንጫ ድንጋይ ውኃ ያፈለቅህ
አባታችን ተክለሃይማኖት
አማልደን በኃጢአት እንዳንሞት(፪)