መዝሙር ( የያሬድ ዉብ ዜማ ድንግል እመቤቴ) April 29, 2018


 የያሬድ ዉብ ዜማ ድንግል እመቤቴ ስጦታዬ ነሽ / ፪/
 በምን አንደበቴ እንዴትስ ባለ ቃል ማርያም ልበልሽ/ ፪/

ምድርና ሰማዩ ተአምሽን ይንገሩ
ፍጥረታት በሙሉ ስለ አንቺ ይመስክሩ
ተነግሮ የማያልቅ ድንቅ ነው ስራሽ
ድንግል ሆይ እናቴ አምሳያ የለሽ
 ማርያም ድንግል እረዳቴ
 የምትደርሺልኝ ነይ ስልሽ በጭንቀቴ
 ታምርሽንም በአይኔ አይቻለሁ
 ጽዮን ሆይ ስልሽ ድንግል ሆይ እጠግባለሁ

መዝሙር (በእፀ መስቀል) March 25, 2018


 በእፀ መስቀል ላይ በዚያ አደባባይ (፪)
 አምላክ ሆይ ጌታ ሆይ ተንገላታህ ወይ
 አምላክ ሆይ ጌታ ሆይ መከራ አየህ ወይ

መስቀል አሲዘው ኪሪያላይሶ ወደ ጎልጎታ ኪሪያላይሶ
ሲገርፉህ ሲያዳፉህ ኪሪያላይሶ ስትንገላታ ኪሪያላይሶ