መዝሙር (የሕይወትን መዝገብ) May 26, 2018


 የሕይወትን መዝገብ ቃሉን ያስነበቡህ
 የተዋሕዶ አርበኞች ቅዱሳን ዋኖችህ
 የድካም ዋጋቸው የእምነታቸው ፍሬ
 ያማረ ነውና ምሰላቸው ዛሬ

ምሥጢሩ ምንድነው ድል የማድረጋቸው
ለሰማያዊው ክብር አክሊል ያበቃቸው
የሕይወታቸውን መዝገብ ግለጥና አንብበው
መፍትሔ አለውና ገድላቸው የአበው

መዝሙር (ሞገድ ሲመታኝ ማዕበሉ) May 6, 2018


 ሞገድ ሲመታኝ ማዕበሉ
  ሞን ያድነዋል ሁሉም ሲሉ
  በሰላም አለፍኩ በፀጥታ
  ሁሉ ተችሎ በአንተ ጌታ(2)

በአንተስ ቁስል ተፈወስኩኝ
ጌታ በፍቅርህ ተማረኩኝ
ሞቴን ሽረኸው በአንተ ሞት
ይሄው አቆምከኝ በህይወት(2)