የአገልጋይ መንፈሳዊ ባሕርያት

የካቲት 27ቀን 2007ዓ.ም.

 

ይህ የትምህርት መርሐ ግብር በማኅበረ ቅዱሳን በአዲስ አበባ ማእከል የአባላት ማስተባበሪያ ዋና ክፍል አዘጋጅነት እየተዘጋጀ በየሳምንቱ የሚቀርብ ትምህርት ነው፡፡ በዚህ ትምህርት መርሐ ግብራችን የአገልጋዮችን በሕብረት የመሆን ጥቅምና የአገልጋይን ባሕርያት በሚመለከቱ ጉዳዮች ላይ ይሆናል ፡፡

 

ክፍለ ትምህርት አንድ

         

ምዕራፍ አንድ:-  አገልጋዮች በሕብረት ሆነው የማገልገላቸው ዓላማ፡-...

ሰበር ዜና:- በዝቋላ ገዳም ዳግም የእሳት ቃጠሎ ተቀሰቀሰ

አትም

የካቲት 25 ቀን 2007 ዓ.ም.

በእንዳለ ደምስስ

abune gebre menfes kidus 01 በደብረ ከዋክብት ዝቋላ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ አንድነት ገዳም በዛሬው እለት ከቀኑ 5፡00 ሰዓት ጀምሮ በምሥራቅ አቅጣጫ በሚገኘው ደን ዳግም የእሳት ቃጠሎ መቀስቀሱ ከገዳሙ አባቶች ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡


በትናንትናው እለት ተቀስቅሶ የነበረው እሳት ከፍተኛ ርብርብ ተደርጎ ጠፍቶ የነበረ ቢሆንም በዛሬው እለት ተቀሰቀሰውን እሳት ለማጥፋት በገዳማውያኑ ከፍተኛ ጥረት እየተደረገ ይገኛል፡፡ በአሁኑ ሰዓት እሳቱ ደኑን እያወደመ በከፍተኛ ሁኔታ እየተቀጣጠለ እንደሚገኝ የገለጹት ገዳማውያኑ ከደብረ ዘይ...

የሆሳዕና ደብረ ገነት ቅድስት ድንግል ማርያም ቤተ ክርስቲያን ተቃጠለች

001 hosaen mariam

የካቲት 23 ቀን 2007 ዓ.ም.

በዘማች አዩኔ /ከሆሳዕና ማእከል/

 በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በሀድያ እና ስልጤ ሀገረ ስብከት የሆሳዕና ደብረ ገነት ቅድስት ድንግል ማርያም ቤተ ክርስቲያን የካቲት 21 ቀን 2007 ዓ.ም ከቅዳሴ በኋላ ድንገተኛና ለጊዜው መንስኤው ባልታወቀ ሁኔታ ተቃጠለች፡፡...

ምኩራብ(የዐቢይ ጾም ሦስተኛ ሳምንት)

የካቲት 20 ቀን 2007 ዓ.ም.

የዕለተ ሰንበት መዝሙር (ከጾመ ድጓ)

ቦአ ኢየሱስ ምኩራበ አይሁድ ወመሐረ ቃለ ሃይማኖት ወይቤሎሙ ምጽዋተ አበድር እመሥዋዕት አነ ውእቱ እግዚኣ ለሰንበት ወአቡሃ ለምሕረት እግዚኣ ውእቱ ለሰንበት ወልደ እጓለ እመሕያው ኢትግበሩ ቤተ አቡየ ቤተ ምስያጥ ቤትየሰ ቤተ ጸሎት ይሰመይ ቦአ ምኩራቦሙ ወገሠፆሙ ያርምሙ አንከሩ ምህሮቶ ሞገስ ቃሉ ወጣዕመ ነገሩ ወሣዕሣዓ አፉሁ፡፡...

ምኩራብ

 

 የካቲት 20 ቀን 2007.ም.

መ/ር ሳሙኤል ተስፋዬ    

እንደ ቤተክርስቲያናችን ሥርዓትና ትውፊት መሠረት በዐቢይ ጾም ስምንቱ ሰንበታት ሊዘመር የተዘጋጀው የጾመ ድጓው መዝሙር ነው፡፡ በየሰንበቱ የሚነበቡት የመጽሐፍ ቅዱስ ምንባባት ፣ የሚዘመረው የዳዊት መዝሙር (ምስባክ) ከሰንበቱ ስያሜ ጋር የሚያያዙና የሚዛመዱ ናቸው፡፡ በሰንበታቱ ውስጥ የሚነበበውና የሚዘመረውም ጌታችን በመዋዕለ ስብከቱ ያስተማራቸውን ትምህርቶችና የሠራቸውን ዋና ዋና ተዓምራትና መንክራት የሚመለከቱ ናቸው፡፡ ጾሙ የጌታ ጾም ስለሆነ ሁሉም መዝሙራትና ምንባባት ከጌታ ትምህርትና ሥራ...

የማኅበረ ቅዱሳን ቴሌቪዥን ሥርጭት በሰሜን አሜሪካ ግዛቶች እያደገ መሆኑ ተገለጸ

አትም

የካቲት 19 ቀን 2007 ዓ.ም.

001 mk logoበመ/ር ሳሙኤል ተስፋዬ

 በኢቢኤስ /EBS/ በመሠራጨት ላይ የሚገኘው የማኅበረ ቅዱሳን የቴሌቪዥን መርሐ ግብር በሰሜን አሜሪካ በሚገኙ ሦስት ግዛቶች በቦስተን፤ በካምብሪጅ እና ሲያትል ይተላለፍ የነበረውን ሥርጭት በማሳደግ አራተኛውንና አምስተኛውን ሥርጭት በመንትያ ከተሞች /twin cites/ በሚናፖሊስ እና ሴንት ፖል ግዛቶች የካቲት 15 ቀን 2007 ዓ.ም. ሥርጭት መጀመሩን የማኅበሩ የኅትመትና ኤሌክትሮኒክስ ሚዲያ ዋና ክፍል ሓላፊ ዲያቆን ዶክተር መርሻ አለኸኝ ገለጹ፡፡...

 

 

 

በዓለ ጥምቀት በጎንደር ከተማ

img 3695

ጥር 12 ቀን 2007 ዓ.ም.

ዲ/ን ዘአማኑኤል አንተነህ /ከጎንደር ማእከል/

 ቤተ ክርስቲያን በዓለ ጥምቀትን የምታከብረው የበዓሉን ጥንታዊነት በጠበቀ መልኩ ሲሆን፤ ሀገራችን በዓለም እንድትታወቅና የበርካታ ጎብኝዎች መስሕብ እንድትሆን አድርጓታል፡፡ እንደመታደል ሆኖ ጎንደር ደግሞ የሊቃውንት መፍለቂያ ከመሆኗም በተጨማሪ ጥምቀት በድምቀት ይከበርባታል፡፡


የ2007 ዓ.ም. አከባበሩም የሚከተለውን ይመስል ነበር፡-...

የጥምቀት በዓል በድምቀት ተከበረ

dscn4684

ጥር 11 ቀን 2007 ዓ.ም.

በእንዳለ ደምስስ

 የ2007 ዓ.ም. የጥምቀት በዓል ጥር 11 ቀን በመላው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በድምቀት ተከበረ፡፡...

በሦስተኛው ቀን በገሊላ ቃና ሠርግ ሆነ

kana zegelila 07

ጥር 11 ቀን 2007 ዓ.ም

መ/ር ምሥጢረ ሥላሴ ማናየ

ወአርአየ ስብሐቲሁ ወአምኑ ቦቱ አርዳኢሁ  ጌትነቱን ገለጠ ደቀ መዛሙርቱም በእርሱ አመኑ” ዮሐ. 2፤11 በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የበዐላት አከባበር ቀመር ከበዓለ ልደት ፤ግዝረት፤ ጥምቀት ቀጥሎ ቃና ዘገሊላ ይከበራል፡፡ ምክንያቱም ክብር ምስጋና ይግባውና ጌታችን አምላካችን መድሃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የሰውን ልጅ ለማዳን ወደዚህ ዓለም በመጣበት ወቅት ልዩ ልዩ የሆኑ ድንቅ ተአምራት አድርጓል፡፡ ከእነዚህም የመጀመሪያው በቃና ዘገሊላ በሰርግ ቤት ተገኝቶ ያደረገው ተአምር ተጠቃሽ...

ወተጠሚቆ ሶቤሃ ወጽአ እማይ ጌታችን … ከተጠመቀ በኋላ ከውሃው ወጣ

timket 01-07

ጥር 10 ቀን 2007 ዓ.ም.

ሊቀ ሊቃውንት ዕዝራ ሐዲስ 
የአራቱ ጉባኤያት መምህርና የጎንደር መ/መ/መድኃኔ ዓለም ቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪ

 በነቢያት የተነገረው ትንቢት በወንጌል የተጻፈው የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ በዓለ ጥምቀት ከተሥአቱ ከዘጠኙ ታላላቅ በዓላት አንዱ ነው፡፡ጥምቀት ተጠምቀ ተጠመቀ ካለው ግሥ የወጣ ሲሆን ጥምቀት ማለት በውሃ መጠመቅና በወራጅ ወንዝ በሐይቅ ውስጥ በምንጭ የሚፈጸም ነው:: በካህናት እጅ የሚፈጸመው ጥምቀት ከሌላው ጥምቀት ልዩ ነው::...

የከተራ በዓል

የከተራ በዓል

08 ቀን 2007 ዓ.ም.

መ/ር ሳሙኤል ተስፋዬ

 የጥምቀት በዓል በኢትጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን በታላቅ ድምቀት ይከበራል፡፡ የጥምቀት በዓልን በአደባባይ በማክበር የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ብቸኛዋ ቤተክርስቲያን ናት፡፡ በሀገር ቤትና በውጭ የሚገኙ የእምነቱ ተከታዮች፣ ከተለያዩ ዓለማት የበዓሉ ታዳሚ ለመሆን ወደ ኢትዮጵያ የመጡ ቱሪስቶች ወደ ጥምቀት በዓል ማክበሪያ ቦታዎች ይሄዳሉ፡፡ ...

በዳጋ እስጢፋኖስ ገዳም ደን ላይ የእሳት ቃጠሎ ደረሰ

daga 001

• እሳቱ የጠፋው ከቤተ ክርስቲያኑ በግምት በ50 ሜትር ርቀት ላይ ነው

ጥር 7 ቀን 2007 ዓ.ም.

በባሕር ዳር ማእከል

 በጣና ኃይቅ በሚገኘው በዳጋ እስጢፋኖስ ገዳም ደን ላይ ጥር 6 ቀን 2007 ዓ.ም ረፋድ ላይ የእሳት ቃጠሎ ደረሰ፡፡...

ቅድስት ሥላሴ

ቅድስት ሥላሴ

ጥር 6 ቀን 2007 ዓ.ም.

በመ/ር ተስፋሁን ነጋሽ

 “ሥላሴ” የሚለው ቃል “ሠለሰ፤ ሦስት አደረገ” ከሚለው የግእዝ ግሥ የተገኘ ሲሆን ትርጉሙ ሦስት ማለት ነው፡፡ ይህን ሦስትነት ለጌታ ስንቀጽለው “ልዩ የሆነ ሦስትነት” የሚለውን ፍቺ ያመላክታል፡፡...

በአርባ ምንጭ ደብረ ጽዮን ቅድስት ማርያም ገዳም የተገነባው የአብነት ትምህርት ቤት ርክክብ ተካሔደ

arba

ጥር 5 ቀን 2007 ዓ.ም.

በደመላሽ ኃይለ ማርያም

 በአርባ ምንጭ ደብረ ጽዮን ቅድስት ማርያም ገዳም የተገነባው የአብነት ትምህርት ቤት ብፁዕ አቡነ ኤልያስ  የጋሞ ጎፋ እና የደቡብ  ኦሞ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ  በተገኙበት ጥር 3 ቀን 2007 ዓ.ም ርክክብ ተካሔደ፡፡...

ግዝረት

ጥር 5/2007ዓ.ም

ግዝረት ከጌታችን ከመድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ዘጠኙ ንዑሳን በዓላት አንዱ ነው፡፡ እነዚህ ንዑሳን በዓላት የሚባሉትም ስብከት፣ ብርሃን፣ ኖላዊ፣ ግዝረት፣ ቃና ዘገሊላ፣ ልደተ ስምዖን፣ ደብረ ዘይት፣ የመጋቢት መስቀልና መስቀል ናቸው፡፡ ነቢያት ይወርዳል፤ ይወለዳል ብለው በትንቢት ይጠባበቁት የነበረው መሲሕ የዓለም ብርሃን፣ የነፍሳት ጠባቂ መሆኑን አምነን የምናከብራቸው ስብከት፣ ብርሃንና ኖላዊ ይባላሉ፡፡...

የብፁዕ አቡነ አረጋዊ ሥርዓተ ቀብር ተፈጸመ

23

ጥር 1 ቀን 2007 ዓ.ም.

በእንዳለ ደምስስ

 የብፁዕ አቡነ አረጋዊ የመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል የበላይ ሓላፊ ሥርዓተ ቀብር ጥር 1 ቀን 2007 ዓ.ም. ከቀኑ 9፡00 ሰዓት ከ1992 ዓ.ም. ሲያገለግሉበት በነበረው በዚሁ ካቴድራል ቅዱስ ፓትርያርኩ፤ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት፤ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የመምሪያ ሓላፊዎች፤ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያንና ምእመናን በተገኙበት ተፈጸመ፡፡...

ብፁዕ አቡነ አረጋዊ ዐረፉ

ብፁዕ አቡነ አረጋዊ ዐረፉ

ጥር 1 ቀን 2007 ዓ.ም.

 

በእንዳለ ደምስስ

23 ብፁዕ አቡነ አረጋዊ የመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል የበላይ ጠባቂና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል በተለያዩ የመንግሥትና የግል ሆስፒታሎች ሕክምና ሲደረግላቸው ቆይቶ ጥር 1 ቀን 2007 ዓ.ም. ጧት በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ዐረፉ፡፡

 

ሥርዓተ ቀብራቸው በዛሬው እለት ከቀኑ 9፡00 ሰዓት በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ይፈጸማል፡፡

 

ዝርዝር የሕይወት ታሪካቸው እንደደረሰን እናቀርባለን፡፡

 ...

ቀጠሮው በደረሰ ጊዜ እግዚአብሔር ልጁን ላከ፤ ከሴትም ተወለደ /ገላ. 4፣4/

xmas

ታኅሣሥ 28 ቀን 2007 ዓ.ም.

በመ/ር ሳሙኤል ተስፋዬ

 እግዚአብሔር አምላክ ዓለምንና በውስጧ ያሉትን ፈጠረ ዘፍ 1፡1 ሌሎች ፍጥረታት ለአንክሮ ለተዘክሮ ሲፈጠሩ ሰውና መላእክት ግን መንግሥቱንና ክብሩን ይወርሱ ዘንድ ተፈጠሩ፡፡...

“ለገጠር አብያተ ክርስቲያናት እንድረስላቸው›› በሚል መሪ መልእክት ሐዋርያዊ ጉዞ ተካሄደ::

20153 1

መ/ር ሳሙኤል ተስፋዬ 

 

ታኅሣሥ 26 ቀን 2007 ዓ.ም.

 በማኅበረ ቅዱሳን አዳማ ማዕከል፣ የደብረ ዘይት ወረዳ ማዕከል ‹‹ለገጠር አብያተ ክርስቲያናት እንድረስላቸው›› በሚል መሪ ቃል ምዕመናንን ያሳተፈ ሁለተኛውን ሐዋርያዊ ጉዞ ታህሳስ 26 ቀን 2007 ዓ.ም በጠንቁ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን አካሄደ፡፡...