የአቡነ ጎርጎሪዎስ ካልዕ ምኞት በነቅዓ ጥበብ አቡነ ጎርጎሪዎስ ትምህርት ቤት እየተተገበረ ነው፡፡

አትም

መ/ር ሳሙኤል ተስፋዬ

ታኅሣሥ 25 ቀን 2007 ዓ.ም.

አቡነ ጎርጎሪዎስ ካልዕ ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ሐዋርያዊ አገልግሎት ከፍተኛ ጥረት ያደርጉ ነበር፡፡ ምኞታቸውና ጥረታቸው ከነበረው አንዱ ህጻናት ቤተክርስቲያናቸውን ቀርበውና አውቀው እንዲያገለግሏት ማድረግ ነበር፡፡img 19201...

1ዐ.4 ቦ / አለ/ በመራሕያን ሲረባ/ Verb to have/

ግእዝን ይማሩ 

ታኅሣሥ 24 ቀን 2007 ዓ.

1ዐ.4 ቦ / አለ/ በመራሕያን ሲረባ/ Verb to have/

ብየ= አለኝ  ምሳሌ  ምንት ብየ ምስሌኪ    ካንቺ ጋር ምን አለኝ

ብከ= አለህ         ምንት ብከ ምስሌሃ   ከርሷ ጋር ምን አለህ

ብኪ = አለሽ       ምንት ብኪ ምስሌሃ   ከርሷ ጋር ምን አለሽ

ብነ = አለን        ምንት ብነ ምስሌክሙ  ከእናንተ ጋር ምን አለን...

ዳገቱን መወጣት ግድ የሚለው የስብከተ ወንጌል አገልግሎት

abune markos gojam

ታኅሣሥ 23 ቀን 2007 ዓ.ም.

 •    ብፁዕ አቡነ ማርቆስ የምሥራቅ ጐጃም ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ እና በጠቅላይ ቤተ ክህነት የስብከተ ወንጌል መምሪያ የበላይ ሓላፊ ከስምዐ ጽድቅ ጋዜጣ ዝግጅት ክፍል ጋር ያደረጉት ቃለ ምልልስ

 

 ቤተ ክርስቲያናችን እምነቷን፣ ሥርዓቷንና ትውፊቷን ከምታስተላልፍባቸው መንገዶች አንዱና ዋነኛው የስብከተ ወንጌል አገልግሎት ነው፡፡ ከጥንት ጀምሮ እግዚአብሔር ታላላቅ ነቢያትን፤ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያንን እያስነሣ ሲመክር፣ ሲገሥጽ፣ እውነተኛውን መንገድ በአባቶቻችን ላይ አድሮ ሲመራ...

ዋሻ አምባ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ገዳም

urael

  ታኅሣሥ 8 ቀን 2007 ዓ.ም.

መ/ር ሳሙኤል ተስፋዬ

ጅብና የነብር መንጋዎች እማሆይን ሳያተናኮሉ ያላምዷቸው ነበር፡

 

“ሳልማር ማንበብ ቻልኩ”

 

በደን ልማት፣ በባዮ ጋዝና በትጋታቸው ከታዋቂ ኢትዮጵያውያን ሴቶች ጋ ሥራቸው ቀርቧል፡፡


ክፍል አንድ


ከአዲስ አበባ ወደ ባሕር ዳር የሚወስደውን የአስፋልት መንገድ ይዘው ሲጓዙ ፍቼ፣ ደብረ ጉራቻ፣ጎሀ ጽዮን ከተሞችን አልፈው የዓባይን በረሃ ካጠናቀቁ በኋላ የደጀን ከተማን ያገኛሉ፡፡ ጉዞዎን በመቀጠል ......

የማቴዎስ ወንጌል

 

ታኅሣሥ 7 ቀን 2007 ዓ.ም.

ምዕራፍ 11

ዮሐንስ መጥምቅ በግዞት ቤት ሳለ ጌታችን ያደረገውን ተአምራት፣ ያስተማረውን ትምህርት ሰምቶ “ትመጣለህ ብለን ተስፋ የምናደርግህ አንተ ነህ? ወይስ ተስፋ የምናደርገው ሌላ አለ?” ብላችሁ ጠይቁ ብሎ ከደቀመዛሙርቱ ሁለቱን ላከ፡፡ ስማቸውም አካውህ እና እስጢፋኖስ ይባላል፡፡ እኒህ ሁለቱ ተጠራጥረው ስለነበር አይተው አምላክነቱን ይረዱት ብሎ ነው እንጂ እርሱ ተጠራጥሮ አይደለም፡፡ ማቴ.14፡3፣ ዘዳ.18፡18፣ ዮሐ.6፡14፡፡...

በዓታ ለማርያም

በዓታ ለማርያም

ታኅሣሥ 3 ቀን 2007 ዓ.ም.

በዲ/ ታደለ ፈንታው


ይህ ዕለት የልዑል እግዚአብሔር እውነተኛ መቅደስ የምትሆን እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ወደ ቤተ መቅደስ የገባችበትን ዕለት የምናስብበት ነው፡፡ የአምላክ እናት ከእናት ከአባቷ ቤት ተለይታ እግዚአብሔር ወደመረጠላት ሥፍራ ወደ ቤተ መቅደስ ገባች፡፡ ዕድሜዋ ሦስት ዓመት ነበር፡፡...

ጥንታዊ ጽሑፎችን ለመጠበቅ በቅንጅት መሥራት እንደሚገባ ተገለጸ

wongel 03

ታኅሣሥ 2 ቀን 2007 ዓ.ም.

በእንዳለ ደምስስ


ጥንታዊ ጽሑፎችን ለመጠበቅና ለተከታዩ ትውልድ ለማስተላለፍ እንዲቻል ባለ ድርሻ አካላት በቅንጅት መሥራት እንደሚገባቸው ኅዳር 29 ቀን 2007 ዓ.ም. በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቤተ መዛግብትና ቤተ መጻሕፍት ኤጀንሲ በቀረቡ ጥናቶች ተገለጸ፡፡...

ዛሬም ያልታጠፉ እጆች ያልዛሉ ክንዶች

aba mef1

 ኅዳር 24 ቀን2007 ዓ.ም. 

 መ/ር ሳሙኤል ተስፋዬ

 

በደቡብና በሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከቶች የቅዱስ ጳውሎስን “ዕለት ዕለት የሚከብድብኝ መልእክት በተግባር የሚኖሩ፤ ከግማሽ ምዕተ ዓመት በላይ ንጹህ ስንዴን የዘሩ ትጉህ መምህር፣ ቀናዒ ለሃይማኖታቸው ፣ በርቱዕ አንደበት መምከርን፣ በትጋት ማስተባበርን፣ ከሚዘምሩት ጋር መዘመርን፣ ከሚያመሰግኑት ጋር ማመስገንን፣ ከሚያዝኑትም ጋር ማዘንን ግብር አድርገው፤ እንደ ሕፃን ከሕፃናት ጋር፣ እንደ ወጣት ከወጣቶች ጋር እንደ አበው ደግሞ ከሊቃውንት ጋር ተዋሕደው ቤተክርስቲያን እያገለገሉ ይገኛሉ::...

“ኦ ገብርኄር ወምእመን ዘበውኁድ ምእመነ ኮንከ ዲበ ብዙኅ እሠይመከ” ማቴ. ፳፭፥፳፫

አንተ በጎ እና ታማኝ አገልጋይ

ኅዳር 15 ቀን 2007 ዓ.ም.

በመ/ር ሳሙኤል ተስፋዬ

ልዑል እግዚአብሔር አምላካችን በነቢዩ አንደበት አድሮ፤ “እከሥት በምሳሌ አፉየ፤ ወእነግር አምሳለ ዘእምትካት፤ አንደበቴን /ነገሬን/ በምሳሌ እገልጣለሁ፤ ከቀድሞ ጀምሮ የነበረ ታሪክና ምሳሌ እናገራለሁ” አለ፡፡ ይህም ማለት ወንጌልን በምሳሌ አስተምራለሁ፤ በመልከ ጼዴቅ ዘመን አስቀድማ የተሠራችና ታይታ የጠፋችውን ወንጌልን እናገራለሁ፡፡ ይህን ታላቅ ምሥጢር ሐዋርያው ሲያብራራ “. . . ከመ በአሚን ያጸድቆሙ እግዚአብሔር ለአሕዛብ አቅደመ አሰፍዎቶ ለአብርሃም ከመ ቦቱ ይ...

1ዐ.2 የአንዳንድ አገናዛቢ አጸፋዎች ዝርዝር

 ዳር 12 ቀን 2007 ዓ.ም.

በመ/ር ደሴ ቀለብ
በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የፊሎሎጂ መምህር

ካልእ = ሌላ፣ ካልእከ / ሌላህ/፤ ካልእኪ የሌላሽን
ቀደምት =/የቀድሞ ሰዎች/፤ ቀደምትክሙ / የቀድሞ ሰዎች የሆኗችሁ ለእናንተ/
ክልኤ = ሁለት፣ ክልኤሆሙ / ሁለታቸው/፤ ክልኤነ / ሁለታችን /፤ ክልኤክሙ / ሁለታችሁ/

በበይናት = በመካከል እርስ በርስ፤ በበይናቲነ/ እርስ በርሳችን /፤ በበይናቲሆሙ / እርስ በርሳቸው/፤ በበይናቲክሙ / እርስ በርሳችሁ/...

ማኅበረ ቅዱሳን በትግራይ ሦስት ገዳማት የተገበራቸውን ፕሮጀክቶች አስመረቀ

gundagundi 02

•ለፕሮጅክቶቹ ማስፈጸሚያ ከ3 ሚሊዮን 180 ሺሕ ብር በላይ ወጪ ሆኗል፡፡ 

ኅዳር 11 ቀን 2007 ዓ.ም.


በእንዳለ ደምስስ


ማኅበረ ቅዱሳን በቅዱሳት መካናት ልማትና ማኅበራዊ አገልግሎት አማካይነት በምሥራቃዊ ትግራይ ሀገረ ስብከት በደብረ ገሪዛን ጉንዳጉንዲ ቅድስት ማርያም፤ በሰሜን ምዕራብ ትግራይ ሽሬ እንዳሥላሴ ሀገረ ስብከት በአስገደ ጽምባላ ወረዳ በአቡነ ቶማስ ደብረ ማርያም ዘሃይዳ፤ በምሥራቃዊ ትግራይ ሀገረ ስብከት በማቅናት አጽቢ ወምበርታ ወረዳ በደብረ ቅዱሳን ዲቦ ቅድስት ማርያም አንድነት ገዳማት ያከናወናቸውን ፕሮጀክቶች አስመረቀ፡፡
...

አምስት የቅዱሳን መዲና የሆኑ ገዳማትን ለመደገፍ ውይይት ተካሄደ

mitaq 1

 መ/ር ሳሙኤል ተስፋዬ 

ኅዳር 12 ቀን 2007 ዓ.ም.

 

 

በሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት  አምስቱ የቅዱሳን መዲናዎች በመባል የሚታወቁት ገዳማት በተለይ ከ1950ዎቹ ጀምሮ  ቅዱሳኑ በቤተ ክርስቲያን  ለምእመናን እየተገለጡ፤ ድምጽ   እያሰሙ፣  ያስተምሩ፣ ይገስጹ፣ ይመክሩ፣ መጻዒውን ያመለክቱ እንደነበር ኅዳር 8 ቀን 2007 ዓ.ም በደብረ መንክራት ሚጣቅ ቅዱስ አማኑኤል ገዳም ገዳማቱን ለመርዳት   በተደረገው የምክክር ውይይት ለመረዳት ተችሏል፡፡

 

 

 

 

 

 

 ...

በአንድ ባለ ሀብት የተሠራው ሕንፃ ቤተ ክርስቲያን ተመረቀ

haro 01

ኅዳር 10 ቀን 2007 ዓ.ም.


በእንዳለ ደምስስ


በደቡብ ምዕራብ ሸዋ ሀገረ ስብከት በሶዶ ዳጪ ወረዳ በአንድ ባለ ሀብት የተሠራው የሀሮ ቅዱስ በዓለ ወልድ ሕንፃ ቤተ ክርስቲያን በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትየጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት እና በብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት ኅዳር 7 ቀን 2007 ዓ.ም. ተመረቀ፡፡...

ከ2004- 2007 ዓ.ም. በደቡብ ኦሞ ሀገረ ስብከት 16,630 አዳዲስ አማንያን ተጠመቁ

jinka tim02 2

 ኅዳር 8 ቀን 2007 ዓ.ም.

በእንዳለ ደምስስ


የደቡብ ኦሞ ሀገረ ስብከት ከማኅበረ ቅዱሳን ጋር በመተባበር ከ2004- 2007 ዓ.ም. 16,630 አዳዲስ አማንያንን በማስተማር መጠመቃቸውን የሀገረ ስብከቱ ሥራ አስኪያጅ አስታወቁ፡፡...

የሐዊረ ሕይወት መርሐ ግብር በደብረ ሊባኖስ ገዳም ይካሔዳል

hawire h 003

 

ኅዳር 8 ቀን 2007 ዓ.ም.

በእንዳለ ደምስስ


ማኅበረ ቅዱሳን ለ7ኛ ጊዜ ያዘጋጀውን የሐዊረ ሕይወት መርሐ ግብር ታኅሣሥ 12 ቀን 2007 ዓ.ም. በደብረ ሊባኖስ አቡነ ተክለ ሃይማኖት አንድነት ገዳም እንደሚያካሒድ የማኅበሩ ምክትል ዋና ጸሐፊና የመርሐ ግብሩ አስተባባሪ አቶ ግርማ ተሾመ ገለጹ፡፡...

የጀበራ ማርያም አንድነት ገዳምን ዳግም ለማቋቋም ጥረት በመደረግ ላይ መሆኑ ተገለጸ

jebera 01

ጥቅምት 29 ቀን 2007 ዓ.ም.

በእንዳለ ደምስስ


በሰሜን ጎንደር ሀገረ ስብከት በደምቢያ ወረዳ በጣና ሐይቅ ውስጥ በ1335 ዓ.ም. ተገድማ የነበረችው የጀበራ ማርያም አንድነት ገዳም ከፈረሰች ከበርካታ ዘመናት በኋላ ዳግም ለማቋቋም ከፍተኛ ጥረት እየተደረገ መሆኑን ገዳሙን መልሶ ለማቋቋም በማስተባበር ላይ የሚገኙት አባ ዘወንጌል ገለጹ፡፡...

“ከዚያ እሰበስባቸዋለሁ፤ ስሜም ይኖርበት ዘንድ ወደ መረጥሁት ሥፍራ አመጣቸዋለሁ” /መጽ.ነህ.1፤9/

gefersa1

 ጥቅምት 28 ቀን 2007 ዓ.ም.

በእንዳለ ደምስስ

  •  “በአንድ ወቅት ክርስትና ለማስነሳት ሌሊት ወደ ገፈርሳ ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ስንሔድ የጅብ መንጋ መጥቶ ክርስትና የሚነሳውን ሕጻን በልቶብናል /የገፈርሳ ጉቼ መካነ ቅዱሳን ቅዱስ በዓለ ወልድ አባ ኪሮስ ወአባ ሳሙኤል ዘዋልድባ ቤተ ክርስቲያን አጥቢያ ምእመናን/



በምዕራብ ሸዋ ሀገረ ስብከት በገፈርሳ ወረዳ ጉቼ ቀበሌ ከአዲስ አበባ ታጠቅን አልፎ ወደ ሆለታ በሚስደው መንገድ የሚገኙ ምእመናን ለረጅም ዘመናት ቤተ ክርስቲያን ሳይኖራቸው እዚህ ዘመን ላይ ደርሰዋል፡፡ በአቅራቢያቸውም ሥርዓተ አምልኮ...

በመስቀል በዓል መጨመር ወይም መቀነስ የሌለበት የትኛው ነው?

meskel 001

 መስከረም 20 ቀን 2006 ዓ.ም.


በዲ/ን ፍቃዱ ዓለሙ



የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ጥንታዊት፣ ሐዋርያዊትና ታሪካዊት እንደ መሆኗ፣ ሁሉም ሃይማታዊ በዓላት ከመንፈሳዊ ባህላዊ ሥርዓቶች ጋር ተሣሥረው እንዲከበሩ መሠረት ናት፡፡ ለዚህ ነው ከሀገራዊና ከሃይማታዊ በዓላት ጋር ተያይዘው የሚከናወኑት መንፈሳዊና ባሕላዊ ሥርዓቶች ምንጫቸው/መነሻቸው/ ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን ናት የምንለው፡፡ ቀድሞም በኦሪቱ በኋላም በሐዲሱ ሕግጋት ጸንታ የቆየች የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ትምህርተ ወንጌልን በመላው ኢትዮጵያ ተዟዙራ አስ
...

አገባቦች (Prepositions and Conjunctions)

መስከረም 14 ቀን 2007 ዓ.ም.

መ/ር ደሴ ቀለብ
በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የፊሎሎጂ መምህር

 1. አቢይ አገባብ፣ አገባቦች ማለት ብቻቸውን ሊነበቡ የማይችሉ መስተዋድዶች ናቸው፡፡ እነዚህም እስመ፣ አምጣነ፣ አኮኑ / Since, because, for/ እመ / ቢሆንም/፣ እስከ፣ እንዘ/ ሲ፣ስ/ አመ/ ጊዜ/ ሶበ/ ጊዜ/

እንተ፣ ዘ፣ እለ /የ/ ወ/እና/ የመሳሰሉት ናቸው፡፡...