ቅዳሴ፣ ማሕሌት፣ ኪዳን፣ ምህላ እና ንግሥ

* ዓመቱን በሙሉ ኪዳን ይደርሳል (6:00 A.M)

* ዘወትር እሑድ ቅዳሴ ይቀደሳል

* በሥላሴ፣ በመድኃኔዓለም፣ በማርያም፣ በሚካኤል እና በዮሐንስ ወርኃዊ በዓላት ይቀደሳል (የክርስትና ማንሳት አገልግሎት ይሰጣል)

* ጥርና ሐምሌ ሥላሴ፣ ጥቅምት እና መጋቢት መድኃኔዓለም፣

      ኅዳር እና ሰኔ ሚካኤል፣ ሰኔና መስከረም ዮሐንስ ይነግሣል

* በጾመ ፍልሰታ የሱባኤ ወቅት ሰዓታት ይቆማል፣ ውዳሴ ማርያምና ቅዳሴ ማርያም ይተረጎማል፣ ቅዳሴ እና የሰርክ ጸሎት ይደርሳል

* በአዲስ ዓመት (በዘመን መለወጫ)፣ በልደት  በትንሣኤ እና ቤተ ክርስቲያናችን ባሏት ተጨማሪ ዐበይት በዓላት የተለያዩ መርሐ-ግብሮች ይከናወናሉ።

* በሰሞነ ሕማማት ከሰኞ እስከ ቅዳሜ ሙሉ አገልግሎት ይሰጣል

ክርስትና

የቤተ ክርስቲያናችን የጥምቀተ ክርስትና አገልግሎት በየዓመቱ እየጨመረ ነው።

¨ ቤተ ክርስቲያናችን ተመርቆ አገልግሎት መስጠት ከጀመረበት ጀምሮ በ፳፻፯ .(Year 2015) ሃምሳ የሚሆኑ ሕፃናት ክርስትና ተነስተዋል

¨ በ፳፻፰ ዓ.ም. (Year 2016) ሃያ ለሚሆኑ ሕፃናት የጥምቀተ ክርስትና አገልግሎት ተሰጥቷል።

ስብከተ ወንጌል እና መንፈሳዊ ትምህርት

* ዘወትር አርብ ስብከተ ወንጌል ይሰጣል

* ዘወትር ቅዳሜ መላ ምእመናንን የሚያሳትፍ የሰንበት ትምህርት ቤት መርሐ-ግብር ይደረጋል

* ዘወትር ቅዳሜ የአብነት ትምህርት እና መሠረታዊ የአማርኛ ቋንቋ ለወጣቶችና ለታዳጊ ሕፃናት ይሰጣል

* ዘወትር እሑድ ሃይማኖታዊና የሥነ-ምግባር ትምህርት ለሕፃናት እና ለወጣቶች ይሰጣል

ዕድር

* የቤተ ክርስቲያናችን አባላት የሆኑ ብቻ በአባልነት ተመዝግበው በኀዘናቸው ጊዜ መርጃ እንዲሆናቸው ታስቦ የተቋቋመው ዕድር ለአባላት አገልግሎት በመስጠት ላይ ይገኛል። 

ለከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ለኮሌጅ እና ዪኒቨርስቲ ተማሪዎች 

* ዘወትር ቅዳሜ በከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ፣  በኮሌጅ እና ዪኒቨርስቲ የቀለም (ዘመናዊ) ትምህርት በመከታተል ላይ ለሚገኙ ተማሪዎች ለሚያነሱት ጥያቄዎች በሙሉ፤ በተለይም የከበዳቸውን እና የተለያዩ የትምህርት ተቋማትን አስመልክቶ ጥያቄ ቢኖራቸው የምክር እና የትምህርት አገልግሎት (mentoring & tutoring programs) ይሰጣል።

 

በወ/ ዘመናይ ዘሪሁን

 

* በአዲሱ የኦባማ ሕግ መሠረት ማንኛውም  ነዋሪ የጤና ኢንሹራንስ (Health Insurance) ሊኖረው ይገባል። በመሆኑም አሠሪዎች ለሠራተኞች  በዓመቱ መጨረሻ 1095C  ወይም  1094 C ፎርም ይልካሉ። ያም ፎርም አሠሪው ለሠራተኛው በቂ ኢንሹራንስ እንዲኖረው ማድረጉንና ሠራተኛውም ምን ያህል እንደተጠቀመ ለIRS ሪፖርት ያደርግበታል።

* በቀረበው ሪፖርት ላይ ሠራተኛው ሙሉ ዓመት የኢንሹራንስ ተጠቃሚ መሆን ሲገባው በተለያዩ ምክንያቶች የግማሽ ዓመት ብቻ ኢንሹራንስ  ካስገባ የዓመቱ ተመላሽ ታክስ ላይ ቅጣት ይኖረዋል።

* ኦባማ ኬር ኢንሹራንስ (Obamacare) በትንሹ $9.00 በሳምንት በመክፈል ማግኘት ይቻላል። ይህም ክፍያ እንደ ገቢዎ መጠን ይወሰናል። በስልክ ቁጥር 1-800-909-0428 ቢደውሉ የመጠየቂያ  ፎርሙን ማግኘት ይችላሉ።

* ከኢሚግሬሽን ቢሮ (US Citizenship and Immigration office ) የነዋሪነት መታወቂያ እንዴት ማግኘት እንደሚችሉ ጥያቄ ቢኖርዎ በስልክ ቁጥር 1-800-375-5283  በመደወል ማነጋገር ይችላሉ።

* አፓርትመንት የሚፈልግልዎት ካምፓኒ ቢያስፈልግዎ በስልክ ቁጥር 1-888-658-7368 በመደወል ማነጋገር ይችላሉ።

በወ/ ዘመናይ ዘሪሁን